የቢንያም መሐመድ ክስና M15 | ኢትዮጵያ | DW | 19.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቢንያም መሐመድ ክስና M15

ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኪር ስታርማን ትናንት እንዳሉት ቢ በሚል ፊደል የሚጠራዉ የብሪታንያ የሐገር ዉስጥ የስለላ ድርጅት M15 ባልደረባ በሕግ የማይጠየቀዉ የተከሰሰበትን ወንጀል የሚያረጋግጥ መረጃ ሥላልተገኘበት ነዉ።

default

ቢንያም መሐመድ

የትናንቱን ዜናችንን የተከታተላችሁ እንደምታስታዉሱት የቀድሞዉ የኹዋንታናሞ እስረኛ ኢትዮጵያዊዉ ቢንያም መሐመድ በእስር ላይ በነበረበት ወቅት ለተፈፀመበት ግፍ በአባሪ ተባባሪነት የከሰሰዉ አንድ የብሪታንያ የሥለላ ድርጅት ባልደረባ በሕግ እንደማይቀጣ የብሪታንያ ጠቅላይ አቃቢ ሕግ አስታዉቋል።ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ኪር ስታርማን ትናንት እንዳሉት ቢ በሚል ፊደል የሚጠራዉ የብሪታንያ የሐገር ዉስጥ የስለላ ድርጅት M15 ባልደረባ በሕግ የማይጠየቀዉ የተከሰሰበትን ወንጀል የሚያረጋግጥ መረጃ ሥላልተገኘበት ነዉ።የሕግ አስተንታኞች ግን የአቀቤ ሕጉን ምክንያት አይቀበሉትም።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ