የቢትልስ የሙዚቃ ቡድን እድገት በሃምቡርግ | ባህል | DW | 05.07.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

የቢትልስ የሙዚቃ ቡድን እድገት በሃምቡርግ

በሃያኛዉ ክፍለ ዘመን አንድ ነጥብ ሶስት ቢሊዮን የሙዚቃ አልብምን በመሸጥ በአለም ደረጃ እጅግ ተወዳጅነትን ስላተረፉት ዘቢትልስ ተብለዉ ስለሚታወቁት እንግሊዛዉያን የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኞች ታሪክ በዛሪዉ ባህል ማድረካችን በጥቂቱ ለመቃኘት ተዘጋጅተናል።

default

ዘቢትልስ

ዘቢትልስ የተሰኙት የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኞች በአለም ደረጃ ታዋቂነትን ለማግኘት የጣልዋት የመሰረት ጠተር በአገራቸዉ በእንግሊዝ ሳይሆን እዚህ በጀርመን በሃምቡርግ የወደብ ከተማ እንደሆን ያዉቁ ነበር?
ዘ ቢትልስ የተሰኙትን እንግሊዛዉያን የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኞች የማያዉቅ ሙዚቃ አፍቃሪ የለም ማለት ይቻላል። በተለይ በምእራቡ አለም ዘንድ እጅግ ተወዳጅነትን ያተረፉ ናቸዉ፣ ነገር ግን እነዚህ እንግሊዛዉያን ሙዚቀኞች ምንም እንኻ የሙዚቃ ስራቸዉን በአገራቸዉ በእንግሊዝ ቢጀምሩም እንዲሁም ለህዝብ ቢያቀርቡም በአለም ደረጃ ለመታወቅ የበቁት እዚህ ጀርመን አገር፣ በወደብ ከተማነቷ በምትታወቀዋ በሃምቡርግ እንደ ነበር የሚያዉቀዉ እጅግ በጣም ጥቂቱ ነዉ። ይሐዉም እንደ አ.አ 1960 ዎቹ አምስት እንግሊዛዉያን በሰሜን ምዕራብ እንግሊዝ በምትገኘዉ ከሊቨርፑል ከተማ ጊታራቸዉን እና እና ሌሎች የሙዚቃ መሳርያቸዉን ጭነዉ ወደ ጀርመን ሃንቡርግ ከተማ ይመጣሉ። ነሃሴ 17 ቀን 1960 አ.ም ከእንግሊዝ ሊቨርፑል ከተማ ወደ ጀርመን የመጡት እነዚህ እንግሊዛዉያን ሙዚቀኞች በሃንቡርግ ከተማ የሙዚቃ ትርኢታቸዉን ያሳያሉ። Pete Best, George Harrison, John Lennon, Paul McCartney und Stuart Sutcliffe የሚባል ስያሜ ያላቸዉ ከሊቨርፑል ከተማ የመጡት አምስት ሙዚቀኞች መጀመርያ ወደ ጀርመን ሃንቡር ከተማ መጥተዉ ሙዚቃቸዉን ለህዝብ ሲያሳዩ ይህን ያህል ተወዳጅ እና በአለም ታዋቂዎች ይሆናሉ ብሎ ያሰበ አልነበረም። ዘቢትልስ የተሰኘዉ የእንግሊዙ የሮክ ሙዚቃ ቡድን ከበሮ መቺ የነበረዉ Pete Best የኛ የሙዚቃ እዉቀት በትክክል አሃዱ ብሎ የጀመረዉ ሃንቡርግ መጥተን ዝግጅቶቻችንን ለህዝብ ማሳየት የጀመርን ግዜ ነዉ ሲል ገልጾአል፥

Deutschland Geschichte The Beatles in Hamburg Fans

በሃንቡርግ እ.አ 1966 አ.ም የቢትልስ ሙዚቃ ተመልካች ወጣቶች


ትዉልድ አገራቸዉ በሆነዉ በሊቨርፑል ከተማ ምንም ሳይታወቁ በጀርመን በሃምቡርግ ሳንት ፓዉሊ በተሰኘዉ ቦታ ታላቅ እዉቅናን ማግኘታቸዉ በጣም የሚገርም ነዉ። ሳንት ፓዉሊ በሃንቡርግ የሚገኝ የመንደር ስያሚ ሲሆን? ይህ መንደር በተለይ በርካታ የዳንኪራ ቤቶች እና መጠጥ ቤቶች የሚገኙበት ዕጽ በድብቅም ሆነ በግልጽ የሚሸጥበት፣ ሴተኛ አዳሪዎች በብዛት የሚገኙበት በተለይ ለሊቱ ደምቆ የሚነጋበት መንደር በመሆኑ ይታወቃል። ዘ ቢትልስ የተሰኙት አምስት የእንግሊዝ የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኞችም በዚሁ መንደር ሙዚቃቸዉን በቀን ከ6-8 ሰአት ያለማቃረጥ በቀን በቀን በማሳየት በዝያ ግዜዉ የጀርመን መገበያያ ገንዘብ በቀን ሰላሳ ዴ ማርክ እያንዳንዳቸዉ ያገኙ ነበር። በተለይ ኢንዲራ ተብሎ በሚታወቀዉ የምድር ቤት መጠጥ ቤት ዉስጥ የሚያሳዩት የሙዚቃ ትርኢት ለሊቱን፣ ስምንት ሰአት ቆመዉ ያለማቋረጥ ያሳዩ ያዜሙ ስለነበር ስራዉ አድካሚ እንደ ነበር ይገልጻሉ። ለድካም መቋቋምያ ቀዝቃዛ ቢራ ይጠቱ እንደነበር ይናገራሉ። ጥንካሪ የሚሰጥ መድሃኒት ይወስዱ እንደነበርም አልካዱም። በሃምቡርግ በሳንት ፓዉሊ መንደር ለሊቱን ትርኢታቸዉን አሳይተዉ ቀን እረፍት የሚያደርጉበት አንድ ጥራት ያልነበረዉ ክፍል በጣም ጠባብ እና በድርብርብ አልጋላይ ይተኙ እንደ ነበር Paul McCartney ይተርካል , Paul McCartney በመቀጠል የምንኖርበት ክፍል በርግጥ በጣም አስቂኝ አይነት ነበረች፣ ትዝ የሚለኝ አንድ ጽዳት የጎደላት ሽንት ቤት አጠገብም ነበረች ይላል። በ 1960 ዎቹ ዘ ቢትልስ የተባሉት እንግሊዛዉያን የሮክ ሙዚቃ አቀንቃኞች አስቸጋሪ እና ስነ-ምግባር የጎደላቸዉ ወጣት የሙዚቃ ቡድኖች እንደ ነበሩ ይነገራል። በመጠጥ ቤት በብድር ጠጥተዉ ባለመክፈላቸዉ፣ እንዲሁም መንገድ ላይ አንዳንድ ለየት ያለ ምግባር የጎደለዉ ነገር ሲሰሩ በፖሊሶች ብዙ ግዜ መያዛቸዉ እና ማስጠንቀቅያ ይደርሳቸዉ እንደነበር ተዘግቦአል። በዝያን ዘመን ቆንጆና በጣም ለጋ የነበሩት ዘቢትልስ የሙዚቃ ቡድኖች አንዳንድ ግዜ የሙዚቃ ትርኢታቸዉን በሚያሳዩበት ወቅት ተመልካቹን ይሰድቡም እንደ ነበር ተዘግቦአል። በመድረክ ላይ አንዳንድ ወቅት በዉስጥ ሱሪ ብቻ መድረክ ላይ ይቀርቡ እንደነበር ወይም የዘመናዊዉ የሽንት ቤት ክዳን አንገታቸዉ ላይ አጥልቀዉ ትርኢታቸዉን አሳይተዉም ነበር። በመድረክ ላይ ሲወጡ ቆሽሰዉ ሲወርዱ ደግሞ መድረክ አቆሽሸዉ የሚለዩት ዘ ቢትልስ የሙዚቃ ባንዶች አገር ወዳድነታቸዉን ለማሳየት ግን የእንግሊዝ ባንዲራ ተለይቶአቸዉ አያዉቅም ነበር። ከሁለተኛ አለም ጦርነት ወዲህ ወግ አጥባቂ ሆኖ የቆየዉ በርካታዉ የጀርመን ህዝብ ይህን አይነቱን የመድረክ አቀራረብ አልተቀበለዉም ነበር፣ ምንም እንኻ ለየት ያለዉ የሮክ ሙዚቃ አቀራረባቸዉ ታዋቂነትን እያተረፈላቸዉ ቢመጣ፣ ባንጻሩ ግን ለወጣቱ ማለት ከሁለተኛ አለም ጦርነት በኻላ ለተፈጠረዉ አዲሱ ትዉልድ ግን፣ ቢትልሶች የዘመኑ ኮከብ ሙዚቀኞች ሆኑ።
በሃምቡርግ የዳንኪራ መድረክ ታዋቂ ከያኒ ሆንን፣ ድንቅ የሆነ የመድረክ ቅንብርና ሙዚቃም ለአፍቃሪዎቻችን ማቅረብ ጀመርን ሲል Pete Best የተባለዉ ሌላዉ የቢትልስ የሮክ ሙዚቃ ቡድን ባልደረባ መግለጹ ተጠቅሶአል። ቢትልሶች የሙዚቃ አቀራረባቸዉ እየተሻሻለ በሃምቡርግ በጣም ተወዳጅነታቸዉ በጣም እየጠነከረ መጣ። ከዝያም የመጀመርያ የሙዚቃ አልበማቸዉን ገበያ ላይ አዋሉ። My Bonnie is over the ocean ከተሰኘዉ የሙዚቃ አልብም በዝያኑ ወቅት በጀርመን የሙዚቃ መዘርዝር በተወዳጅነቱ የአምስተኛ ደረጃን ያዘ።

Deutschland Hamburg Beatles-Platz eingeweiht

በሃንቡርግ የቢትልስ አደባባይ


ዘ ቢትልስ የሙዚቃ ቡድን እንደ አ.አ 1962 አ.ም የመጨረሻዉን ትርኢታቸዉን አሳይተዉ ሃንቡርግን ለቀቁ። ከዝያም ነዉ በአለም የሙዚቃ መድረክ ትርኢታቸዉን ማሳየት የጀመሩት
እንደ አዉሮፓዉያኑ አቆጣተር 2008 አ.ም ማለትም ባለፈዉ አመት ዘ ቢትልስ የተሰኘዉ የሙዚቃ ቡድን ሙዚቃ ለህዝብ ማቅረብ በጀመረበት በጀርመኗ ሃምቡርግ ከተማ ዉስጥ ጀርመናዉያን ለነዚህ በአለም ተደናቂ ለሆኑት የእንግሊዝ የሙዚቃ ቡድኖች ታዋቂነትን ለማትረፍ ጠጠር በጣሉባት ከተማ ለአራቱ የቡድኑ አባላት ማለት ለHarrison, ለLennon, ለMcCartney እና ለ Starrከማይዝግ ብረት የተቀረጸ የማስታወሻ ሃዉልት ተሰርቶላቸዉ ባለፈዉ አመት የከተማይቱ ከንቲባ መርቀዉታል። ከነዚህ ከአራቱ የቢትልስ የሮክ የሙዚቃ አቀንቃኞች ሃዉልት ትንሽ ራቅ ብሎ ደግሞ ለአምስተኛዉ የቢትልስ ባንድ አባል ለSutcliffe,እንዲሁ ተሰርቶለታል ከአራቱ ለየት ብሎ የቆመበት ምክንያትም በአዉሮፓዉያኑ 1962 አ.ም በዝያዉ በሃንቡርግ ሳለ በጭንቅላቱ ዉስጥ የደም መፍሰስ እክል አጋጥሞት በእንጭጩ ስለተለየም ነበር። ታድያ ዘ ቢትልስ የተባሉት የእንግሊዝ የሮክ የሙዚቃ ባንድ ለመጀመርያ ግዜ በህዝብ ዘንድ ለመወደድ በበቁበት በሃምቡርግ ለዝያዉም ሳንት ፓዉሊ ተብሎ በሚታወቀዉ ደማቅ መንደር ከሃምሳ አመታት በኻላ ዛሪም የጀርመኗ ሃምቡርግ ከተማ ለሙዚቃ ባንዱ ፍቅሯን ለመግለጽ የሙዚቀኞቹን ምስል የሚገልጽ የማስታወሻ ሃዉልት በማቆም ታሪክን ማዉሳትን ይዛለች።
በሙዚቃ ከኢትዮጽያ ጥላሁን ገሰሰ ፣ ከጀማይካ ቦብማርሊ፣ ከአሜሪካ ማይክል ጃክሰን በአለም ህዝብን በጥሩ ቅላጼያቸዉ የአፍቃሪዎቻቸዉን ልብ እንዳስኮበለሉ ሁሉ ከእንጊሊዝም ዘ ቢትልስ የተሰኙት የሙዚቃ ባንዶች የአገሪቷ የክብር መጠርያም ናቸዉ። ከአምስቱ ሙዚቀኞች መካከል ግን በህይወት የሚገኙት የድራም ማለት ከበሮ ተጫዋቹ እና ድምጻዊዉ እና በግራ እጁ ጊታር መመምታቱ የሊታወቀዉ የቢትልስ የሙዚቃ ባንድ ባልደረባ McCartney ነዉ። በለንደን አገር እነዚህ ቡድኖች አብዛኛዉን የሙዚቃ አልብማቸዉን የተቀዱበት ስቱድዮ በአሁኑ ወቅት የባንዱ ሙዝየም ሆኖ ሙዚቃ ሲያሳዩ ይለብሱዋቸዉ የነበሩት አልባሳት የሙዚቃ መሳሪያዎቻቸዉ እንዲሁም የተለያዩ ፎቶግራፎቻቸዉ የሚታይበት ሆንዋል። በቤቱ የዉጭ ግድግዳ ላይ ደግሞ፣ ከአለም አገራት ይህንን የሙዝየም ለመጎብኘት የመጡ ቱሪስቶች ፊርማቸዉን እያኖሩበት ይሄዳሉ።

Azeb Tadesse