የቡድን 7 ጉባዔ በቶርሚና ኢጣልያ  | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 26.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

የቡድን 7 ጉባዔ በቶርሚና ኢጣልያ 

በቡድን 7 የሚጠቃለሉት በኢንዱስትሪ የበለፀጉት ሰባቱ የዓለም ሃገራት በደቡባዊ ጣልያን በሲሲሊ ደሴት የቶርሚና ከተማ ዛሬ ጉባዔያቸዉን ጀምረዋል። የዩኤስ አሜሪካ፤ የጃፓን፤ የካናዳ፤ የፈረንሳይ፤ የብሪታንያ፤የኢጣልያ እና የጀርመን መንግሥታት ተጠሪዎች በሁለት ቀናቱ ጉባዔያቸዉ በተለይ በደኅንነት ጉዳይ ፖለቲካ ላይ እንደሚመክሩ ተገልፆአል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:30

ስብሰባዉ ተጀምሯል፤

ብሪታንያ ማንችስተር ላይ የሽብር ጥቃት መድረሱን ተከትሎ ጉባዔዉ ሽብርተኝነትን መዋጋት» የሚለዉን ርዕሱ እንደሚያደርግ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ጉባዔዉ አጨቃጫቂ የተባሉትን የንግድ ልዉዉጥና የአየር ንብረት ለውጥ ርዕሶችንም ያነሳል። በቡድን ሰባት ጉባዔ ላይ ለመጀመርያ ጊዜ የሚሳተፉት አዲሱ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሃገራቸዉ አምና ፓሪስ ላይ ከፈረመችዉ የሙቀት አማቂ ስጋቶች ቅነሳ ስምምነት እንደምትወጣ እና በብሔራዊ ፍላጎት ላይ ያተኮረ የንግድ ፖለቲካ ላይ እንደምታተኮር ተናግረዋል። ይህን ጉዳይ በተመለከተ ግን የዩኤስ አሜሪካ መንግሥት እስካሁን ምንም ዓይነት ዉሳኔ አላስተላለፈም።  በኢጣልያ የሮም ወኪላችን ተኽለዝጊ ገብረየሱስ ዛሬ ቶርሚና ላይ ስለተጀመረዉ የቡድን ሰባት ጉባዔ ዘገባ ልኮልናል። 

ተኽለዝጊ ገብረየሱስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ 

Audios and videos on the topic