የቡድን ስምንት ዓቢይ ጉባዔ እና ትፅቢቱ | ዓለም | DW | 06.06.2007
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቡድን ስምንት ዓቢይ ጉባዔ እና ትፅቢቱ

ከፍተኛ ጥበቃ የሚደረግበት የቡድን ስምንት መንግሥታት መሪዎች ዓቢይ ጉባዔ ዛሬ ማምሻውን

ሜርክልና ቡሽ በሀይሊገንዳም

ሜርክልና ቡሽ በሀይሊገንዳም

ከምሥራቅ ጀርመናዊቱ የሮስቶክ ከተማ ሀያ አምስት ኪሎሜትር ርቃ በምትገኘው በሃይሊገንዳም ከተማ ይከፈታል። እስከፊታችን ዓርብ የሚቆየውና ጀርመን፡ ዩኤስ አሜሪካ፡ ብሪታንያ፡ ፈረንሳይ፡ ኢጣልያ፡ ካናዳ፡ ጃፓን እና ሩስያ የሚጠቃለሉበት የኃያላኑ መንግሥታት መሪዎች የሚያካሂዱት ጉባዔ በበርካታ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት አጀንዳ ይዞዋል።

ዛሬ ማምሻውን የሚከፈተው የቡድን ስምንት ጉባዔ በማዕከላይነት ሊወያይባቸው ያስቀመጣቸው ዋነኞቹ አጀንዳዎች በዓለም አየር ፀባይ ላይ የሚታየው ለውጥ የደቀነውን መዘዝ የማስወገዱና በአፍሪቃ ሁነኛ መሻሻል ለማስገኘት በአህጉሩ የሚታየውን ድህነት የመቀነሱ ጥረት፡ እንዲሁም፡ ዓለም አቀፍ አጽናፋዊ የኤኮኖሚ ትስስር እና ንግድ የሚሰኙት ጉዳዮች ናቸው። አስተናጋጅዋ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እሰፊታችን ዓርብ ድረስ በሚካሄደው ዓቢይ ጉባኤ ላይ እአአ በ 2012 ዓም የሚያበቃውን የኪዮቶ ውልን የሚተካውን አዲስ ውል ማርቀቅ የሚቻልበትን ሁኔታ ማነቃቃት ይፈልጋሉ ተስፋ አድርገዋል። ጀርመን በምታቀርበው ሀሳብ መሰረት፡ እስከ 2050 ዓም ድረስ ወደ ክበበ አየሩ የሚበተነው የተቃጠለ አየር መጠን እአአ በ 1990 ዓም ከነበረው በሀምሳ ከመቶ ዝቅ እንዲል ነው የተጠየቀው። የኪዮቶ ውል እአአ እስከ ድረስ የተቃጠለው አየር መጠን ከአስራ ሰባት ዓመት በፊት ከነበረው መጠን በአምስት ከመቶ ቅናሽ ብቻ ነበር የጠየቀው። ይሁንና፡ ይኸው የጀርመን ሀሳብ ብዙውን የተቃጠለ አየር የምታወጠዋ ዩኤስ አሜሪካ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆንዋን የቡሽ የተፈጥሮ አካባቢ ጉዳዮች አማካሪ ኮኖውት አስታውቀዋል።
« በዚሁ ሀሳብ ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነን፡ አንድ የጋራ ዓላማ በመድረሱም ጉዳይ ላይ ግልጽ መሆን ይኖርብናል። ያ ዓላማም በአጭር ጊዜ ብሎም በሚቀጥሉት አስርና ሀያ ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ይሆናል። ይህም የእያንዳንዱ ሀገር መንግሥት ዓላማውን ከግብ ለማድረስ እንደሚመቸው በሚያበረክተው ድርሻ ይከናወናል። »
መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በዓቢዩ ጉባዔ ወቅት ስምንቱ መንግሥታት እአአ በ 2005 ዓም በግሌንኢግልስ ስኮትላንድ በብሪታንያ መሪነት በተካሄደው የቡድን ስምንት ዓቢይ ጉባዔ ላይ የልማቱን ርዳታ እአአ እስከ 2010 ዓም ድረስ በእጥፍ ለማሳደግ የገቡትን ቃላቸውን እንደሚጠብቁ እንዲያረጋግጡላቸው ለመጣር ተነሳስተዋል። ጀርመን የልማቱን ርዳታ እአአ በ 2008 እና በ 2011 ዓም መካከል በአራት ቢልዮን ዶላር ለመጨመር እንደምትጨምር አስታውቀዋል። ይሁንና፡ ይህ አባባልዋ የልማቱን ርዳታ በ 2005 ዓም በ 0,5% ለማሳደግ በግሌንኢግልስ የገባቸችውን ቃል ለመጠበቅ እንደማያስችላት አንዳንድ የቡድን ስምንት አባል መንግሥታት የገቡትን ቃል አልመጠበቃቸውን የወቀሱት ብዙ መንግሥታዊ ይልሆኑ ድርጅቶች አስረድተዋል። የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚደንት ጆርጅ ዳብልዩ ቡሽም ሀገራቸው ለኤች አይ ቪ ኤድስ መታገያ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ወደ ሰላሳ ቢልዮን ዶላር ለማእንደሚምታሳድግ አስታውቀዋል። ቡድን ስምንት አባል መንግሥታት በጠቅላላም በአፍሪቃ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመታገሉ ተግባር ተጨማሪ ወጪ በመመደቡ ሀሳብም ላይ መስማማታቸው ግን ገና በውል አልታወቀም። የቡድን ስምንት አባል ሀገሮች ከአፍሪቃ ልዩ ትኩረት መስጠታቸውን ለማጉላትም በማሰብ የግብፅ፡ የአልጀሪያ፡ የሴኔጋልና የደቡብ አፍሪቃ መሪዎችን በዓቢዩ ጉባዔ እንዲሳተፉ ጋብዘዋል። ለአፍሪቃ ይሰጥ የሚባለው የልማት ርዳታ የሕዝቡን ችግር ያቃልላል መለት እንደማይቻል የግብረ ሰናዩ ድርጅት የካሪታስ ኢንተርናሽናል የአፍሪቃ ጉዳይ ተጠሪ ክርስቶፍ ክሊች ኦት እረድተዋል።
« ገንዘብ በመስጠት ደስተኛ ሕዝብ ለመፍጠር አይቻልም፡ ይህን ዓላማ ከግብ ከማድረሱ ተግባር ደግሞ እጅግ ርቀን ነው የምንገኘው። ለዚህም በአውሮጳ እና በሰሜን አሜሪካ ለግብርናው ዘርፍ የሚሰጠው ድጎማን እንድ ምሳሌ መጥቀስ ይበቃል። ጋና ወይም አይቨሪ ኮስት ውስጥ በድጎማ የተመረተ የዶሮ ሥጋን አፍሪቃ ውስጥ በርካሽ ከሚመረተው ባነሰ ዋጋ መግዛት የሚቻልበትና አፍሪቃም በድጎማውና በንግዱ ማከላከያ ርምጃ ሰበብ ምርቶችዋን በበለፀገው ዓለም ገበያዎች መሸጥ የማትችልበት ሁኔታ ትልቅ ችግር ደቅኖባታል። »
ጉባዔው እክል የገጠመው የዓለም አቀፍ የንግድ ውይይትን ለማነቃቃት በጉባዔው በተሳታፊነት ከሚካፈሉት ከጠንካራዎቹ አዳጊ ሀገሮች፡ ማለትም፡ ከብራዚል፡ ከቻይና፡ ከሕንድ፡ ከሜክሲኮና ከደቡብ አፍሪቃ መሪዎች ጋር በንግዱ ዙርያ በሰፊው እንደሚወያይ ይጠበቃል።
በሩስያ እና በዩኤስ አሜሪካ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ዛሬ ማምሻውን በጀርመን የሀይሊንገን ከተማ የሚጀመረውን በኢንዱስትሪ የበለፀጉት መንግሥታት የቡድን ስምንት ጉባዔ ለያዘው የውይይት አጀንዳ ተገቢውን ትኩረት እንዳይሰጥ አስግቶዋል።