የቡድን ሰባት አገሮች ስብሰባ | ዓለም | DW | 05.06.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የቡድን ሰባት አገሮች ስብሰባ

የቡድን ሰባት አባል ሃገራት ፤ በአውሮፓው ህብረት ሰብሰቢነት ብራሰልስ፣ ቤልጅየም ላይ ተሰብስበው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከመምከራቸውም ፣ ጉባዔአቸውን ሲያጠቃልሉ መግለጫ አውጥተዋል። ስምንተኛ አባል

የነበረቸውን ሩሲያን ያገለሉት የምዕራባውያን መንግሥታት መሪዎች፤ ከ 70 ዓመት በፊት ፤ በናዚ ጀርመን ላይ የዘመቱት የ 2ኛው የዓለም ጦርነት ተጓዳኝ ሃገራት ከምዕራብ በኩል ጦራቸውን በኖርማንዲ በኩል ያስገቡበትን ዕለት ነገ በፈረንሳይ አስተናጋጅነት ያስቡታል። በዚሁ ክብረ በዓል እንዲገኙ የተጋበዙት የሩሲያው ፕሬዚዳንት እንደሚሳተፉ ከወዲሁ ተገልጿል። የቡድን ሰባት አባል ሀገራትን ስብሰባና ውሳኔ በተመለከተ የ ብራሰልሱን ዘጋቢአችንን ገበያው ንጉሤን በስልክ አነጋግሬው ነበር።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic