የቡድን ሰባት ሚንስትሮች ስብሰባ | ዓለም | DW | 15.04.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቡድን ሰባት ሚንስትሮች ስብሰባ

የዩናይትድ ስቴትስሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ግን በስብሰባዉ ላይ የተካፈሉት ለሰወስት ሰዓት ያክል ብቻ ነዉ።የቡድን ሰባትን ዓላማና መርሕ የሚቃወሙ ወገኖች ደግሞ ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ሉቤክን በሰልፍና ዳንኪራ ሞልተዋት ነበር።

ቡድን-7 የተሰኘዉ ማሕበር የሚያስተናብራቸዉ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ሉቤክ-ጀርመን ዉስጥ ያደረጉትን የሁለት ቀን ሥብሰባ ማምሻቸዉን አጠናቅቀዋል። ሚንስትሮቹ የዩክሬንን ቀዉስ፤ የኢራንና የምዕራባዉያንን ስምምነት፤የየመን ጦርነት፤የእስላማዊ መንግሥት (ISIS)ና ሌሎችንም «የሠላምና የፀጥታ» ያሏቸዉን ጉዳዮች አንስተዉ ተነጋግረዋል።ሥብሰባዉ በመጪዉ ሰኔ ለሚደረገዉ የቡድኑ የመሪዎች ጉባኤ የመነጋገሪያ ርዕስ ለማርቀቅ ያለመ ነበር።የዩናይትድ ስቴትስሱ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ጆን ኬሪ ግን በስብሰባዉ ላይ የተካፈሉት ለሰወስት ሰዓት ያክል ብቻ ነዉ።የቡድን ሰባትን ዓላማና መርሕ የሚቃወሙ ወገኖች ደግሞ ካለፈዉ ሰኞ ጀምሮ ሉቤክን በሰልፍና ዳንኪራ ሞልተዋት ነበር። የፈረንሳይ፣

የብሪታኒያ፣ የጀርመን፣ የካናዳ፣ የዩናይትድ ስቴትስ፣ የኢጣልያና የጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሁለት ቀናት ስብሰባቸው ካተኮሩባቸው ጉዳዮች ውስጥ የምሥራቅ ዩክሬኑ ግጭት መፍትሄ ፣ የኢራን የኒክልየር መርሃ ግብር ፣ ራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራውን ቡድን ለመዋጋት መወሰድ ያለባቸው እርምጃዎችና የኤቦላ ወረርሽኝ ይገኙበታል ። የአስተናጋጅዋ የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር ስብሰባው ስለየመኑ ግጭትም እንደሚነጋገር አስታውቀው ነበር ።
«የየመንን ሁኔታ በሚመለከት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ የሄደውን እና በርካታ ሰዎችን ሰለባ ያደረገውን ግጭት ማብረድ በሚቻልባቸው የተለያዩ መንገዶችም ላይ እንነጋገራለን ።»
ሽታይንማየር ባለፉት ዓመታት ስምንተኛ ሃገር ሆና በቡድኑ ስብሰባ ላይ ስትካፈል የቆየችው ሩስያ ቡድኑን እንደገና የመቀላቀል እድል ሊኖራት እንደሚችልም ጠቁመዋል ። ሞስኮ የዩክሬይንዋን ግዛት ክሪምያን በኃይል ገንጥላ ከራስዋ ሃገር ጋር ከቀላቀለች በኋላ የቡድን ሰባት ሃገራት ሩስያን ከጉባኤያቸው አግልለዋል ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ይልማ ሐይለ ሚካኤልን

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic