የቡድን ሥምንት ጉባኤና ኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 18.05.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቡድን ሥምንት ጉባኤና ኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን በጉባኤዉ ላይ መካፈል ዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያንና ከኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ተቃዉሞም፥ ድጋፍም ገጥሞታል።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ARCHIVKOMBO - Die Staats- und Regierungschefs der Gruppe der Acht (G8) 2012 - Obere Reihe (l-r): US-Präsident Barack Obama, der Premierminister von Großbritannien, David Cameron, Bundeskanzlerin Angela Merkel (CDU), und Italiens Regierungschef Mario Monti. Untere Reihe (l-r): Der französische Präsident Francois Hollande, der russische Präsident Dmitri Medwedew, der Premierminister von Kanada, Stephen Harper und der Premierminister von Japan, Yoshihiko Noda. Der G8-Gipfel 2012 findet vom 18.05.2012 bis 19.05.2012 unter US-amerikanischem Vorsitz durch Präsident Barack Obama in Camp David statt. Fotos: dpa (zu dpa-Themenpaket «G8- und Nato-Gipfel in den USA» vom 14.05.2012) +++(c) dpa - Bildfunk+++

ዋንኞቹ ጉባኤተኞች


ቡድን-ሥምንት የተሰኘዉ ማሕበር የሚያስተናብራቸዉ የሥምንቱ በኢንዱትሪ የበለፀጉ ሐገራት መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤ ዛሬ ካፕዴቪድ-ዩናይትድ ስቴትስ ዉስጥ ተጀመሯል።ጉባኤተኞች ከሚወያይባቸዉ ጉዳዮች የኢራንና የሰሜን ኮሪያ የኒክሌር መርሐ-ግብርና ዉዝግቡ፥ የአፍቃኒስታን የወደፊት ሠላም፥ የአዉሮጳ የምጣኔ ሐብት ኪሳራ እና የአፍሪቃ የምግብ ዋስትና ዋንኞቹ ናቸዉ።ሥለ አፍሪቃ የምግብ ዋስትና በሚደረገዉ ዉይይት ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊን ጨምሮ አራት የአፍሪቃ ሐገራት መሪዎች እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የሃገራቸውንና የኢትዮጵያን ግንኙነት ዳግም እንዲያጤኑ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ጠይቀዋል ። የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የተሰኘው ህብረትና የኦክላንድ ተቋም በጋራ ለፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በጻፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ይፈፅሙታል ያሉት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋ ነው ። 2 ቱ ድርጅቶች እንደሚሉት ግን የኦባማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ ዳግም እንደሚያጤነው ኦባማ ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ማስረዳት አለባቸው ። የጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊ በጉባኤዉ ላይ መካፈል ዩናይትድ ስቴትስ ከሚገኙ ኢትዮጵያዉያንና ከኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ተቃዉሞም፥ ድጋፍም ገጥሞታል።የዋሽንግተኑ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic