የቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ታጋቾችን አስለቀቁ | ዓለም | DW | 16.01.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቡርኪና ፋሶ ወታደሮች ታጋቾችን አስለቀቁ

የቡርኪና ፋሶ የጸጥታ ኃይሎች በአል-ቃዒዳ ታጣቂዎች የተያዘውን ሆቴል በማስለቀቅ 126 ታጋቾችን ነጻ አወጡ።

ትናንት በቡርኪና ፋሶ ዋና ከተማ ኡጋዱጉ በሚገኘው ስፕሌንዲድ ቅንጡ ሆቴል ላይ በአል-ቃዒዳ ታጣቂዎች በተፈጸመው ጥቃት እና እገታ 23 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰምቷል።ሟቾቹ የ18 ሀገራት ዜጎች ሲሆኑ የጸጥታ ኃይሎች ሆቴሉን ነጻ ለማውጣት በወሰዱት እርምጃ አራት ታጣቂዎች መገደላቸውን የጀርመን ዜና አገልግሎት ዛሬ ዘግቧል። እገታው ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቀው ዛሬ ማለዳ ሲሆን ታግተው ከነበሩ ሰዎች መካከል ቢያንስ 33 መቁሰላቸው ተሰምቷል። ከአል-ቃዒዳ ጋር ግንኙነት ሳይኖራቸው አይቀርም የተባሉት ታጣቂዎች ወደ ስፕሌንዲድ ሆቴል ከማምራታቸው በፊት በአካባቢው በሚገኝ ካፑቺኖ የተሰኘ ምግብ ቤት ላይ የእሩምታ ተኩስ ከፍተው ነበር።

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ