የቡሩንዲ ሬፈረንደም | አፍሪቃ | DW | 17.05.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

የቡሩንዲ ሬፈረንደም

በቡሩንዲ ፕሬዚደንት ፒየር ንኩሩንዚዛ እንደገና ለር/ብሔርነት እንዲወዳደሩ ሲባል በሕገ መንግሥቱ ላይ በቀረበው ማሻሻያ ላይ በዛሬው ዕለት ውሳኔ ሕዝብ እየተካሄደ ነው። ውሳኔ ሕዝቡ ከጎርጎሪዮሳዊው 2005 ጀምሮ ሀገሪቱን በመምራት ላይ ያሉት ንኩሩንዚዛ ለተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ካስታወቁ ከሶስት ዓመት በኋላ ነው የተካሄደው።

የንኩሩንዚዛ ውሳኔ ያኔ ሀገሪቱን እከፋ የፖለቲካ ቀውስ ላይ መጣሉ ሲታወስ፣ በቀውሱ ሰበብ 1,200 ሰዎች ሲገደሉ፣ ከ400,000 የሚበልጡ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል። የቡሩንዲ ተቃዋሚ ቡድኖች ሕዝቡ ከሬፈረንደሙ እንዲርቅ ጥሪ አስተላልፈዋል። ውሳኔ ሕዝብ በቡሩንዲ ውጥረቱ ይበልጡን እንዲካረር አድርጓል።

አርያም ተክሌ/አፖሊኔር ኒዪሮራ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic