የበርሊን ግንብ የፈረሰበት ሃያኛ አመት በፎቶ | ይዘት | DW | 06.11.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ይዘት

የበርሊን ግንብ የፈረሰበት ሃያኛ አመት በፎቶ

የዛሬ ሃያ-አመት በርሊን ላይ የሆነዉ-ከመሆኑ በፊት ይሆናል ብሎ ማሰብ በርግጥ ሲበዛ ከባድ ነበር።ሆነ

default

ግንቡ

የበርሊን ግንብ የፈረሰበት ሃያኛ አመት በአል ጀርመን ዉስጥ በተለያዩ ሥነ-ሥርአቶች እየተከበረ ነዉ።የግንቡ መፍረስ የጀርመንን ብቻ ሳይሆን የመላዉ አለምን የእስከዚያ ዘመን ምጣኔ-ሐብታዊ፤ ወታደራዊ ፖለቲካዊ ሒደትን በሙሉ ነዉ የለወጠዉ። ከሰባ-ዘመናት በላይ የፀናዉ ኮሚንስታዊ ሥርዓት ከአለም ጨርሶ ባይወገድም ክፉኛ ተሸመድምዷል።በሌላ በኩል የካፒታሊስቱ ሥርዓት የበላይነት ተረጋግጧል።ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት ፍፃሜ በሕኋላ ኑክሌር ያማዝዛል ተብሎ ሲፈራ የነበረዉ የቀዝቃዛዉ ጦርነትም ከበርሊን ግንብ ጋር አክትሟል። የዛሬ ሃያ-አመት በርሊን ላይ የሆነዉ-ከመሆኑ በፊት ይሆናል ብሎ ማሰብ በርግጥ ሲበዛ ከባድ ነበር።ሆነ።የበርሊን ግንብ ፍፃሜ ለአለም የአዲስ ዘመን-አዲስ ስርዓት ብርቀት ነዉ።ከዚያ ለመድረስ ግን ዓለም በርግጥ ብዙ መስዋዕትነት፥ የዘመናት ፖለቲካዊ-ዲፕሎማሲያዊ ሽኩቻ፥ ወታደራዊ ፍጥጫ፥ እና ሌሎች ብዙ መሰናክሎችን ማለፍ ግድ ነበረበት።ብቻ ዘንድሮ-ሃያ አመቱ። ይናገራል ፎቶ----

DW.COM

ተዛማጅ ዘገባዎች