የበርሊን ግንብ ተገነደሰ-ሕዳር 9 1989 | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.11.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የበርሊን ግንብ ተገነደሰ-ሕዳር 9 1989

ተቀናቃኝ ፖለቲከኞቹ በየሚፈልጉ-በየሚያሸንፉበት መንገድ እንዲሆን ከመሻኮት ባለፍ ግን እንዴትና መቼ እንደሚሆን ለየሕዝባቸዉ ትክክለኛዉን መልስ መስጠት አልቻሉም

default

ጎርባቾቭና ሜርክል በሃኛዉ አመት በአል

እኛ አንድ ሕዝብ ነን።ከ1949 ጀምሮ (ዘመኑ በሙሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) የምሥራቁም የምዕራቡም ሕዝብ አንድነትን ያልጠየቀበት-ሥለ አንድነት ያልዘመረበት ጊዜ በርግጥ የለም።የሁለቱ ወገኖች ፖለቲከኞች የኮሚንስት-ካፒታሊስት ተቃራኒ ደጋፊዎቻቸዉም ሁለት የሆነዉ አንድ የጀርመን ሕዝብ የሚመኝ የሚፈክረዉን በየራሳቸዉ መንገድ መጋራታቸዉ አልቀረም ነበር።ተቀናቃኝ ፖለቲከኞቹ በየሚፈልጉ-በየሚያሸንፉበት መንገድ እንዲሆን ከመሻኮት ባለፍ ግን እንዴትና መቼ እንደሚሆን ለየሕዝባቸዉ ትክክለኛዉን መልስ መስጠት አልቻሉም።የዚያን ቀን ግን በሕዝብ ግፊት ሆነ።የበርሊን ግንብ ተገነደሰ።ዛሬ ሃያ-አመቱ።ለሃያ-አመቱ ያፍታ ቅኝት አብራችሁኝ ቆዩ።

ነጋሽ መሐመድ/አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic