የበረሃዋ መርከብ እጣ | ጤና እና አካባቢ | DW | 02.02.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

የበረሃዋ መርከብ እጣ

በአዉስትራሊያ የሚገኙ ግመሎች ምንጫቸዉ ሰሜን አሜሪካ እንደሆነ አንዳንድ ጽሁፎች ይጠቁማሉ። የመጀመሪያዉ የአዉስትራሊያ ግመል በአዉሮጳዉያኑ 1840ዓ,ም ከካናሪ ደሴት ነዉ ይባላል የመጣችዉ።

default

የበረሃዋ መርከብ በአፍጋኒስታን

ቀጣዩ የግመሎች ቡድን ደግሞ በተመሳሳይ የዘመን ቀመር በ1860ዓ,ም አዉስትራሊያን ባሰሱ ተጓዦች አማካኝነት መግባታቸዉ ይነገራል። ተጓዦቹ ግመሎቹን 220 እና 325ማይል ርቀቶችን ምን ዉሃ ሳያጠጡ እንደተጠቀሙባቸዉ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከስድስት ዓመታት በኋላም እንስሳቱን ለማራባት ጥረት ተደረገ። ያም ለ50ዓመታት ያህል ዘልቆ የአዉስትራሊያ የተባለዉን የተለየ የግመል ዘር አስገኘ። ዘራቸዉን ከማዳቀልና ማብዛት በተጨማሪ እስከአዉሮፓዉያኑ 1907ዓ,ም ድረስ በርካሽ ዋጋ በመገኘታቸዉ ከፓኪስታንና ህንድ ሳይቀር በርካታ ግመሎችን አዉስትራሊያ ወደምድሯ ስታስገባ ቆይታለች። በእነዚህ ጊዜያት ዉስጥም ከ10,000 እስከ 12,000 የሚገመቱ ግመሎች አዉስትራሊያ ገብተዋል። በረሃማ በሆነዉ የአዉስትራሊያ አካባቢ ለሸክምም ሆነ ለመጓጓዣ ሲያገለግሉ የቆዩት ግመሎች ትላልቆቹ እስከ600ኪሎ ግራም ሲሸከሙ፤ ትናንሾቹ ከ300 እስከ 400ኪሎ ይጫንባቸዋል። በአዉስትራሊያ የመሰረተ ልማት ግንባታ ግመሎች ያበረከቱት አገልግሎት በዋዛ የሚዘነጋ እንዳልሆነ የሰፈሩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በለማዳነታቸዉ የሰዉ ልጅ መልካም ተጓዳኝ በመሆናቸዉ የሚታወቁት በረሃ የማይበግራቸዉ ግመሎች የስልክ መስመሩ ቢዘረጋ፤ የወርቅ ማዕድኑ ቢቆፈር፤ በየከተማዉም የተለያዩ እቃዎች ሲፈለጉ እዚህም እዚያም ለምሰስቱት አቅማቸዉ ሲባል ይጎተታሉ። በገጠር ለገበሬዎች በከተማ ለነጋዴዎች አስፈላጊዉን ተሸክመዉ የሚቀርቡ ግመሎች ነበሩ።

Indien Sicherheitskräfte reiten auf Kamelen

በህንድ የፀጥታ ኃይሎች የክብር መጓጓዣ

በተለይ ለበረሃማዉ የአዉስትራሊያ አካባቢ የማይዘነጋ አስተዋፅኦ አድርገዋል። ዉሎ አደረና በአዉሮጳዉያኑ 1920ዓ,ም ገደማ የሞተር ተሽከርካሪዎች ለመጓጓዣነትና ለሸክም መጫኛነት እንደዉም ቀልጠፍ ብለዉ በተፈለጉበት በመድረስ የሰዎችን ድካም ሲያቀሉ ግመሎች ወደዳር ይገፉ ጀመር በአዉስትራሊያ። በየቤቱ ለዚሁ አገልግሎታቸዉ ሲባል የታገሩት ግመሎች ተለቀቁና ነፃ የሆነዉን ማኅበረ ግመል በአዉስትራሊያ በረሃማ አካባቢ መሰረቱ። በዓለም ዙሪያ የሚገኘዉ የግመሎች ብዛት በአዉሮጳዉያኑ 1982ዓ,ም 17ሚሊዮን ተገምቷል። አዉስራሊያ ያሏት ደግሞ የዛሬ 17ዓመት የተደረገ ቆጠራና ግምት እንደሚለዉ ከ150ሺ እስከ 200ሺ ይደርሳል። እነዚህ ለሰዉ ልጅ በችግሩ ወቅት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዉ ቴክኒዎሎጂ ወደጫካ የገፋቸዉ የአዉስትራሊያ ግመሎች በየገበሬዉ መንደር በሚያደርሱት ችግር ሞት ተፈርዶባቸዋል። የአዉስትራሊያ ባለስልጣናት በዱር የሚገኙትን ወደ6,000 የሚገመቱ ግመሎች በሄሊኮፕተር አማካኝነት እየነዱ ወደአንድአካባቢ በማሰባሰብ በጠብመንጃ ሊረፈርፏቸዉ መወሰናቸዉ ሲሰማም በርካቶችን ማሳዘኑ አልቀረም። የሳዉዲ መንግስትና ሌሎች የአረብ አገራት ስለበረሃዋ መርከብ ምን ብለዉ ይሆን? በእኛስ ወገኖች ዘንድ ግመል ያላት ስፍራ? ቀጣዮቹ ዘገባዎችን ያዳምጡ፤

ነብዩ ሲራክ፤ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ