የበሕነን ወቀሳ | ኢትዮጵያ | DW | 20.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

 የበሕነን ወቀሳ

የበኒ ሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (በሕነን) የክልሉ መንግሥት ጫና እያደረሰበኝ ነዉ በማለት ወቀሰ።የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት ለDW እንደነገሩት የንቅናቄዉ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተዋል፣ አባሎቻቸዉም ይታሰራሉ፣ይሰደዳሉ፣ይበደላሉም

አውዲዮውን ያዳምጡ። 01:59

የበኒ ሻንጉል መስተዳድር ተቃዋሚ ፓርቲ መስተዳድሩን ወቀሰ


የቀድሞዉ የበኒ ሻንጉል ጉሙዝ አማፂ ቡድን፣ የበኒ ሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (በሕነን) የክልሉ መንግሥት ጫና እያደረሰበኝ ነዉ በማለት ወቀሰ።የንቅናቄዉ ባለሥልጣናት ለDW እንደነገሩት የንቅናቄዉ ፅሕፈት ቤቶች ተዘግተዋል፣ አባሎቻቸዉም ይታሰራሉ፣ይሰደዳሉ፣ይበደላሉም።የክልሉ መስተዳድር ባለሥልጣናት ግን የተቃዋሚዉን ንቅናቄ ወቀሳ አልተቀበሉትም።ቀድሞ ከኤርትራና ሱዳን ይዋጋ የነበረዉ በሕነን በሰላማዊ መንግገድ ለመታገል ወደ ሐገር የገባዉ ከአምስት ዓመት በፊት ነዉ።

ነጋሳ ደሳለኝ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ
 

Audios and videos on the topic