የቆሼ ተጎጅዎች ጉዳይ | ኢትዮጵያ | DW | 26.04.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቆሼ ተጎጅዎች ጉዳይ

ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪቃ  ርዕሠ-ከተማ በምትባለዉ አዲስ አበባ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ ከ110 በላይ ሰዎች ማለቃቸዉ ዛሬም ድረስ እንዳነጋገረ ነዉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:05

የቆሼ ሰለባዎች

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ባለፈዉ መጋቢት 2 ያዋቀሩት ኮሚቴና የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በሕይወት የተረፉ ተጎጅዎችን ለመርዳት እየተንቀሳቀሱ እንደምገኙ ሲዘገብ ቆይተዋል።

ተጎጅዎችን ለመርዳትም ለጋሽ ድርጅቶችና ባለሃብቶች ከ84 ሚሊዮን ብር ቃል ገብተዉ እንደነበር፣ ነገር ግን  ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢ የሆነዉ 60 ሚሊዮን 992 ሺህ ብር መሆኑን የሰራተኛና የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤፍሬም ግዛዉ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል። ተጎጅዎችን ለመርዳት ቢሯቸዉ እንደ እቅድ የያዘዉን አስረድተዉም ነበር።

ቃል የተገባዉ የገንዘብም ሆነ የቁሳቁስ ርዳታ ምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ለመረዳት በአደጋዉ ጊዜ የተጎዱት ግለሰቦችን ወይም ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉትን አነጋግረናል። 
በአደጋዉ የተጎዳ ዉስጥ ጓደኛ አለኝ ያሉን፣ ግን ስማቸዉ እንዳይጠቅስ የፈለጉ ግለሰብ፣ ጓደኛቸዉና ለሎች ተጎጅዎች በቆሼ አካባቢ ወደሚገኘዉ ቀበሌ የወጣት መዝናኛ ዉስጥ ድንኳን ተጥሎላቸዉ እንዲሁም ክፍት ቢሮ ዉስጥ በብዛት አሳርፏቸዉ እንደምገኙ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።

በደረቅ ቆሻሻ የማስወገድ አጋልግሎት ላይ የተሰማራዉ የዳይናሚክ የፅዳት አገልግሎት ድርጅት ስራ አስከያጅ አቶ ሐፍቴ ወልደማርያም ጉዳተኛን  የማፈላለጉ ስራ እንደተጠናቀቀና በአከባብዉ የሚገኙ ሰዎችም «ቤትና መሬት» ተሰቷቸዋል መባሉን ሰምቻዋለዉ ይላሉ።

በዶይቼ ቬሌ የፌስቡክ ደህረ ገፃ ላይ አስተያየታቸዉን ካጋሩን ዉስጥ «የተሰጠዉ ገንዘብ ለተሰጠበት አላማ መዋሉን ወይም አለመዋሉን መቆጣጠር ያስፈልጋል» ያሉ ሲኖሩ «አስከሁን ድረሰ ያለማንም ቀስቃሽና ድጋፍ ህዝቡ ከመንግስት ጎን በመቆም አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ ለይ ይገኛል» ሲሉም አስተያየታቸዉን አጋርተዋል። 


መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic