የቆሻሻ ክምር መደርመስ እና የህዝብ አስተያየት | ኢትዮጵያ | DW | 13.03.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቆሻሻ ክምር መደርመስ እና የህዝብ አስተያየት

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተከመረው የቆሻሻ ተራራ በተደረመሰበት አደጋ የ50 ሰዎች ህይወት መጥፋቱ ብዙዎችን ከማሳዘን አልፎ አስቆጥቷል። ምክንያቱም፣ ዶይቸ ቬለ ያነጋገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አባላት እንደሚሉት፣ ክምሩ አንድ ቀን መደርመሱ እንደማይቀር ማንም የሚያውቀው ነበር።

ሰዎቹ በዚያ ሲኖሩ መንግሥት መከልከል ነበረበት፣ የቆሻሻው ክምር ላያቸው ላይ ሊናድ የሚችልበትን አደጋ ማስከተሉ ስለማይቀር፣  ሰዎቹ የቤት ችግር ቢኖርባቸውም እንኳን፣ በዚያ ሲኖሩ በቸልታ ማየት አነበረበትም በማለት አደጋው እንዳይደርስ መንግሥት አስፈላጊውን የማከላከል ርምጃ ባለመውሰዱ ለሰው ህይወት መጥፋት ተጠያቂ  ነው በሚል ወቀሳ ሰንዝረዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic