የቅሪተ አፅም እድሜ እንዴት ይታወቃል? | ሳይንስ እና ኅብረተሰብ | DW | 23.10.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ሳይንስ እና ኅብረተሰብ

የቅሪተ አፅም እድሜ እንዴት ይታወቃል?

የቅሪተ አፅም እድሜ መለክያዉ እንዴት ነዉ፤ ረጅም እድሜ እንዳለዉ የሚነገረዉ ቅሪተ አፅምስ መገኛ ቦታዉ እንዴት ይታወቃል? ከመቶ ሽ በላይ እድሜ ያላቸዉን ቅሪተ አፅሞች እድሜ መለክያ ዘዴ እጅግ ቀላሉ ነዉ ያሉን ዶክተር ብርሃኔ አስፋዉ ሉሲ «ድንቅነሽ» ስትገኝ ከነበሩ ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ነበሩ።

በዓለም ዉስጥ እጅግ ግዙፍ እድሜ ካላቸዉ አስረ አንድ ቅሪተ አፅሞች መካከል ዘጠኙ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘታቸው ይነገራል ። በምስራቅ ጎጃም ማችክል ወረዳ ነዋሪ የሆኑት አድማጫችን አቶ አማኑኤል ከተማ እባካችሁ፤ ግዙፍ እድሜ እንዳላቸዉ የሚነገርላቸዉ ቅሪተ አፅሞች መገኛ ቦታ እንዴት ይታወቃል? የቅሪተ አፅሙ እድሜስ እንዴት ነዉ የሚለካዉ ብለዉ የላኩልንን ጥያቄ ይዘን በዛሪዉ ዝግጅታችን መልስ የሚሰጡንን ባለሞያ ጋብዘናል።

Die Zeichnung zeigt, wie Ardi ausgesehen haben könnte (undatiertes Handout). Unser ältester Vorfahr war viel weniger affenartig als bisher vermutet. Das zeigt ein sensationeller Fund aus Äthiopien. Ardi, wie die Forscher das weibliche Skelett nennen, ist mit 4,4 Millionen Jahren sogar über eine Million Jahre älter ist als der berühmte Fund Lucy. Ardi war etwa 1,20 Meter hoch, 50 Kilogramm schwer und besaß einzigartige Eigenschaften: Ihre Hände, Füße und ihr Becken deuten darauf hin, dass sie auf Bäumen kletterte, sich aber auch auf zwei Beinen auf dem Boden bewegte. (zu dpa 0417 vom 01.10.2009) ACHTUNG: Verwendung nur im Zusammenhang mit der Berichterstattung und mit Urhebernennung Zeichnung: J.H. Matternes SPERRFRIST 1. Oktober, 20.00 Uhr) +++(c) dpa - Report+++

አርዲ

አርዲ የሚል መጠርያን ያገኘችዉና በአዋሽ ሸለቆ አካባቢ የዛሪ አስራ አንድ ዓመት ግድም የተገኘችዉ የሴት ቅሪት አፅም የዛሪ ሃያ አንድ ዓመት ግድም ስለ ሰዉ ልጅ አመጣጥ ታሪክ የነበረዉን እምነት ማስለወጡን የቅሪተ አካል ተመራማሪዎች በወቅቱ ተናግረዋል፤ አርዲ ስትገኝ። እርዲ እንደ ሉሲ ሙሉ በሙሉ አፅሟ ባይገኝም ሉሲን ግን አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ዓመት እንደ ሚበልጥ ነዉ የተነገረዉ፤ ግን የቅሪተ አጽም እድሜ መለክያዉ እንዴትይሆን? በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሙዚየም ቋሚ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ብርሃኔ አስፋዉ እንደሚሉት፤

ከመቶ ሽ በላይ እድሜ ያላቸዉን ቅሪተ አፅሞች እድሜ መለክያ ዘዴ በተለይ እኛ እና በምስራቅ አፍሪቃ አካባቢ የምንገኝ ተመራማሪዎች የምንጠቀምበት የስሌት ዘዴ ነዉ ሲሉ ዶክተር ብርሃኔ ያስረዳሉ።

በሳይንሳዊ መጣሪያዉ Ardipithecus ramidus የተባለዉ የአርዲ ቅሪተ አጽም ከቺንፓንዚ መሰልነት ዘር ወጣ ያለ ትክክለኛ የሰዉ ዘር ሃረግ ግንድ ላይ ያለ ነዉ ተብሎአል፤ በተመራማሪዎች ። ምንም እንኻ ቅሪተ አፅሙ የዛሪ 21 ዓመት ቢገኝም የምርምሩ ስራ በደንብ ከስር መሰረቱ ሲካሄድ እና ግኝቱ ለዓለም ህዝብ ይፋ እስኪ ሆን 17 ዓመታትን መፍጀቱ ተገልጾአል።

ግን ይህ እድሜ ጠገብ የሆነ ቅሪተ አጽም መገኛ ቦታዉ በምን ይሆን የሚታወቅ ? የሉሲ ቅሪተ አጽም ሲገኝ በምርምሩ ስራ ተካፋይ የነበሩት መካከል አንዱ የነበሩት ዶክተር ብርሃኔ ብርሃኔ አስፋዉ፤ ኢትዮጵያ በስነ ምድር ጥናት እጅግ ከፍተኛ እርምጃን እያሳየች መምጣትዋን የገለፀዉ ፤ በተለይ የጀርመን ተመራማሪዎች ጋር የትብብር ስራ መኖሩን ተናግረዋል። ዶክተር ብርሃኔ አስፋዉ ለሰጡን ቃለ ምልልስ እያመሰገንን ሙሉዉን ቅንብር እንዲያደምጡ እንጋብዛለን!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic