የቄለም ወለጋው ግድያ፣ ኦዲፒ እና የኦነግ ሸኔ | ኢትዮጵያ | DW | 30.05.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቄለም ወለጋው ግድያ፣ ኦዲፒ እና የኦነግ ሸኔ

ከሁለት ቀናት በፊት በቄለም ወለጋ ሙጊ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሽኔ በሚባሉ አባላት ተወረወረ ባለው ቦምብ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል ሲል የዞኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዲፒ ጽሕፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሸማቂዎች የተባሉ ግን ክሱን አስተባብለዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:32

የቄለም ወለጋው ግድያ

በተለያዩ ጊዜያት በምዕራብና ቀለም ወለጋ በሚደርሱት ጥቃቶች መንግሥትና ታጣቂ ቡድኖች አንዳቸው ሌላኛቸውን ተጠያቂ ሲያደርጉ ይሰማል። ከሁለት ቀናት በፊት በቄለም ወለጋ ሙጊ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሽኔ በሚባሉ አባላት ተወረወረ ባለው ቦምብ ስድስት ሰዎች ተገድለዋል ሲል የዞኑ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ኦዲፒ ጽሕፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሸማቂዎች የተባሉ ግን ክሱን አስተባብለዋል። ሰዎቹ የተገደሉበት የሙጊ ቀበሌ ነዋሪዎች ደግሞ ግዲያው የተፈጸመው በመከላከያ ሠራዊት ነው ይላሉ፡፡ በኦነግ ሸኔ እና በመከላከያ ሠራዊት መካከል ከሙጊ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኝ ቀራ በተባለ ስፋራ ግጭት እንደነበረም  ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ነጋሳ ደሳለኝ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic