የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እና በሕይወት የተረፉት ዝርዝር | ኢትዮጵያ | DW | 08.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እና በሕይወት የተረፉት ዝርዝር

በአዲስ አበባ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ላይ ባለፈው ቅዳሜ ነሃሴ 28 ቀን 2008 በደረሰው የእሳት ቃጠሎ አደጋ የ23 ሰዎች ህይወት ማለፉን የኢትዮጵያ መንግሥት ቢያስታውቅም፣ በአደጋው የሞቱትንም ሆነ በሕይወት የተረፉት ታራሚዎች ስም በይፋ አልገለጸም ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:24

በሕይወት የተረፉት ታራሚዎች ዝርዝር


ዛሬ መንግሥት በሕይወት የተረፉትን እና ወደተለያዩ ማረሚያ ቤቶች የተዛወሩትን ስም ይፋ አድርጓል። ሳይሞቱ ሞቱ በሚል ስማቸው በሀሰት በማህበራዊ ድረ ገፆች ወጥቶ የነበሩ አቶ በቀለ ገርባን የመሳሰሉ ግለሰቦች፣ የተረፉት ሰዎች ስም ዝርዝር ከወጣ በኋላ በሕይወት መኖራቸው መረጋገጡን ጠበቃቸው እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አቶ ወንድሙ ኢብሳ ለዶይቸ ቬለ አረጋግጠዋል።


ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic