የቁጫ አቤቱታና አንድነት ፓርቲ | ኢትዮጵያ | DW | 26.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቁጫ አቤቱታና አንድነት ፓርቲ

በደቡብ ክልል የቁጫ ብሄረሰብን በሚመለከት ተደጋጋሚ ችግር እንግልቶችና የሰዉ ህይወትም የጠፋበት በመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ደርሷል ሲል አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ አስታወቀ። የፓርቲዉ አመራር አባላት አካባቢዉን ሄደዉ በመጎብኘትም ዘገባ አቅርበዋል።

በጎረቤት ሃገራት የሚገኙ የተለያዩ ወገኖች ዛሬ በሰላም እየወጡ ይገባሉ ያሉት የፓርቲዉ አመራር በዚህ አካባቢ ግን ለወራት ችግሩ መፍትሄ እንዳላገኘ አመልክተዋል። ዶቼቬለ ስለጉዳዩ ያነጋገው የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በበኩሉ ጉዳዩን መከታተሉንና ችግሩ ተጣርቶም መልስ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ሪፖርት ወደ አካባቢው በመላክ ላይ መሆኑን አስታውቋል ። ጋዜጣዊ መግለጫዉን የተከታተለዉና የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ሃላፊን ያነጋገረው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic