የቀጠለው የየመን ውዝግብ | ዓለም | DW | 05.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የቀጠለው የየመን ውዝግብ

የየመን ተቀናቃኝ ወገኖች ካለፈው የካቲት ወር ወዲህ የቀጠለውን የህዝብ ዓመጽ በድርድር እንዲያበቁ የባህረ ሰላጤ ሀገሮች የትብብር ምክር ቤት ያቀረበውን ሀሳብ የየመን መንግስት እና አንዳንድ ተቃዋሚ ወገኖች መቀበላቸውን አስታወቁ።

default

ምክር ቤቱ መንግስት አስፈላጊውን ተሀድሶ እንዲያደርግ በተጨማሪ አሳስቦዋል። ካለፉት ሰላሳ ሁለት ዓመታት ወዲህ በስልጣን ላይ ያሉት ፕሬዚደንት አሊ አብዱላ ሳሌህ ከስልጣን እንዲወርዱ በመጠየቅ በሀገሪቱ ተቃውሞው አሁንም የቀጠለ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ቢያንስ ሁለት ሰዎች መገደላቸው ተሰምቶዋል።

ነቢዩ ሲራክ

አርያም ተክሌ ሂሩት መለሰ