የቀጠለዉ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ | ኢትዮጵያ | DW | 06.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቀጠለዉ የሙስሊሞች እንቅስቃሴ

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሐይማኖታዊ ነፃነታችን ረግጦአል በማለት በየሳምንቱ ዓርብ የጁምዓ ፀሎትንና ሥግደትን ተከትሎ የሚያሰሙትን ተቃዉሞ ባለፈዉ አርብ ሚያዝያ 25 አላሰሙም ነበር።

ሙስሊሞቹ ተቃዉሞዉን ለአንድ ቀን ያቋረጡት ክርስትያኑ ኢትዮጵያዊ በዓሉን እንዲያከብር እንደሆነ አስታዉቀዋል። ድምጻችን ይሰማ በሚል መርህ ሙስሊሞች ዘወትር አርብ ከሚያደርጉት ጸሎት በኋላ የሚያሰሙትን ተቃዉሞ፤ የስቅለት በዓልን ምክንያት በማድረግ ያቋረጡት ፤ ክርስትያኑን እና ሙስሊሙን ለማጋጨት የሚፈልጉ ወገኖች አጋጣሚዉን እንዳይጠቀሙ በማሰብ እንደሆንም

ገልጾአል። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት በአሸባሪነት ጥርጣሪ ካሰራቸዉ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ መሪዎች ሁለቱ ማለት ሙባረክ አደም እና ካሊድ ኢብራሂም የቀለበት ስነ-ስርአት ማካሄዳቸዉ ተነገረ። ስነ-ስርአቱ የተካሄደዉ በርካቶች በተገኙበት ቃሊቲ እስር ቤት በኬክ ቆረሳ ስነ-ስርአት እና ፤ በኋላም እስረኞቹ በሌሉበት በሆቴል የምሳ ግብዣ እንዲሁም ፤ ቄራ በሚገኘዉ መስጊድ በተደረገ የፀሎት ስነ-ስርዓት እንደሆነ ወኪላችን ዮሃንስ ገ/እግዚአብሄር ከአዲስ አበባ የላከልን ዘገባ ያሳያል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic