የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ ከእስር መለቀቅ፣ | ኢትዮጵያ | DW | 19.12.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ታምራት ላይኔ ከእስር መለቀቅ፣

ቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚንስትርና የመከላከያ ሚንስትር የነበሩት አቶ ታምራት ላይኔ ከ 12 ዓመታት እስር በኋላ ዛሬ ተፈትተዋል። በ 1988 ዓ ም ፣ በተደራራቢ የሙስና ወንጀል ተከሰው፣ ለእሥራት የተዳረጉት አቶ ታምራት ፣ በ2 ክሶች ጥፋተኛ ተብለው 18 ዓመት ጽኑ እሥራት ተፈርዶባቸው ነበር።

default

ያም ሆኖ፣ ታደሰ እንግዳው፣ ከአዲስ አበባ በላከው ዘገባ ላይ እንዳለው በሀገሪቱ ህግ ¾ኛውን የእሥር ዘመኑን በመልካም ሥነ-ምግባር ለፈጸመ፣ የሚሰጠው የአምክሮ ማህረት ታስቦላቸው ፣ ከ 12 ዓመት የእሥራት ጊዜ በኋላ ዛሬ ከእሥር ተለቀዋል