የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሊታሰሩ ነው | ዓለም | DW | 05.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሊታሰሩ ነው

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ወደ እስር ቤት ሊላኩ ነው። የብራዚልዳኞች የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያቀረቡትን ይግባኝ ዛሬ ማለዳ ውድቅ አድርገዋል። ሉላ ዳ ሲልቫ በቀረበባቸው የሙስና ክስ የ12 አመታት ተፈርዶባቸዋል። ዳ ሲልቫ ለብራዚል ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ጉዳያቸውን ሳይታሰሩ ለመከራከር ጠይቀው ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:26

ዳኞች ሉላ ያቀረቡትን ይግባኝ ውድቅ አድርገዋል

የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ወደ እስር ቤት ሊላኩ ነው። ዳኞች የቀድሞው የብራዚል ፕሬዝዳንት ሉላ ዳ ሲልቫ ያቀረቡትን ይግባኝ ዛሬ ማለዳ ውድቅ አድርገዋል። ሉላ ዳ ሲልቫ በቀረበባቸው የሙስና ክስ የ12 አመታት ተፈርዶባቸዋል። ዳ ሲልቫ ለብራዚል ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ ጉዳያቸውን ሳይታሰሩ ለመከራከር ጠይቀው ነበር። የ72 አመቱ ግራ ዘመም ፖለቲከኛ ከጎርጎሮሳዊው 2003-2011 ዓ.ም. ባሉት አመታት በብራዚል ፕሬዝዳንትነት አገልግለዋል። በመጪው ጥቅምት ወር በሚካሔደው የአገሪቱ ምርጫ ዳግም ሊወዳደሩም እቅድ ነበራቸው። ሉላ በሚል የቁልምጫ ስማቸው የሚታወቁት ፖለቲከኛ የቀረበባቸው ክስ እርሳቸውን ከምርጫ ውድድሩ ለማግለል ሆን ተብሎ የተቀነባበረ እና ፖለቲካዊ ግብ ያለው ነው ሲሉ ያጣጥላሉ። በርካታ ብራዚላውያን ሉዊዝ ኢናሲዮ ሉላ ዳ ሲልቫ ለደሆች የወገኑ ፖለቲከኛ አድርገው ያደንቋቸዋል። 
ይልማ ኃይለሚካኤል
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic