የቀድሞው አንድነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀል | ኢትዮጵያ | DW | 07.11.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቀድሞው አንድነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀል

የቀድሞው አንድነት ለፍትህ እና ለዲሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት ባጭሩ)አመራሮች እና አባላት የሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ። አመራሮቹ  እና አባለቱ የአንድነት ፓርቲ በ2007 ዓ.ም ለሁለት ሲከፈል በምርጫ ቦርድ ዕውቅና ተነፍጓቸው የነበሩ ናቸው፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:53

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አባላት የሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ።

ከእነዚህ መካከል የተወሰኑቱ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ መግባታቸውም የሚታወስ ነው፡፡ ቀሪዎቹ አዲስ ፓርቲ ለማቋቋም በእንቅስቃሴ ላይ መቆየታቸውም አይዘነጋም፡፡ ይህንኑ ፓርቲ ለማቋቋም የአደራጅነት ሚና ከወሰዱት ውስጥ 51 ግለሰቦች ከትላንት በስቲያ እሁድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሁን ባለው ነባራዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ አዲስ ፓርቲ ከመመስረት ይልቅ በእንቅስቃሴ ላይ ካሉት ጋር መቀላቀል እንደሚሻል መወሰናቸውን ገልጸው ነበር፡፡  በዚህም መሰረት ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ለመስራት ወስነው ወደ ፓርቲው ከገቡት የቀድሞ የአንድነት አመራሮች ውስጥ ምክትል ተቀዳሚ ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ተክሌ በቀለ፣ የቀድሞ የፓርላማ አባል አቶ ተመስገን ዘውዴ፣ የፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊው አቶ ስዩም መንገሻ እና ከአመራሮቹ አንዱ የነበሩት አቶ ዳንኤል ሺቢሺ ይገኙበታል፡፡ የአመራሮቹን እና አባላቱን ወደ ፓርቲው መቀላቀል በማስመለክት በሰማያዊ ፓርቲ በኩል ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ 

ተስፋለም ወልደየስ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic