የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተፈረደባቸዉ | ኢትዮጵያ | DW | 15.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ባለሥልጣን ተፈረደባቸዉ

በ1970 የጎጃም ክፍለ ሐገር የደርግ አባል የነበሩት መቶ አለቃ እሸቱ ሰባ-አምስት ሰዎችን ገድለዋል፤ ከሁለት መቶ ሃያ የሚበልጡትን ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዉጪ አስረዋል፤ አሰቃይተዋልም የሚል ክስ ተመስርቶባቸዉ ሲከራከሩ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:52

መቶ አለቃ እሸቱ ሰባ-አምስት ሰዎችን ገድለዋል

ኔዘርላንድስ የሚኖሩት የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መንግስት (የደርግ) ከፍተኛ ባለሥልጣን  መቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ በዘመነ ሥልጣናቸዉ ለፈፀሙት በደል ዕድሜ ልክ እስራት ተበየነባቸዉ። በ1970 የጎጃም ክፍለ ሐገር የደርግ አባል የነበሩት መቶ አለቃ እሸቱ ሰባ-አምስት ሰዎችን ገድለዋል፤ ከሁለት መቶ ሃያ የሚበልጡትን ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዉጪ አስረዋል፤ አሰቃይተዋልም የሚል ክስ ተመስርቶባቸዉ ሲከራከሩ ነበር። ዛሬ ዘ-ሔግ ኔዘርላድስ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ተከሳሹ በተያዘባቸዉ የወንጀል ጭብጥ በሙሉ ጥፋተኝነታቸዉን አረጋግጦ እድሜ ልክ ዕስራት ፈርዶባቸዋል። የፍርዱን ሒደት የተከታተለዉን ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋንና አንድ የዓይን ምሥክርን በሥልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic