የቀድሞዉ የሰማያዊ ፓርቲ ባለሥልጣን መከሰስ | ኢትዮጵያ | DW | 09.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የቀድሞዉ የሰማያዊ ፓርቲ ባለሥልጣን መከሰስ

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ምክንያት በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች መታሰራቸዉ ይነገራል። ከእነዚህ ታሳሪዎች መካከል የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግኑኝነት ሃላፊ አቶ ዮናታን ቴስፋዬ ይገኙበታል ።

Äthiopien Addis Abeba Blue Party

በፎቶዉ ላይ መኃል ላይ የተቀመጡት የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ቴስፋዬ፤ በዝያን ወቅት ጋዜጣዊ መግለጫን ሲሰጡ

አቶ ዮናታን ከአራት ወር በላይ ከታሰሩ በዋላ ባለፈዉ ረቡዕ ፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዉ በፀረ-ሽብር አዋጅ ተከሰዋል። እንደ ክሱ ዝርዝር በኦሮሚያ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ አስመልክቶ አቶ ዮናታን በፌስ ቡክ ባወጣቸው ጽሁፎች ፤ ሽብርን በማኅብረቡ መኃል ቀስቅሰዋል በሚል ነዉ። መርጋ ዮናስ ዘገባ አዘጋጅተዋል።

የቀድሞ የሰማያዊ ፓርት የሕዝብ ግኑኝነት አላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ በታሕሳስ ወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ጀምሮ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራዉ እስር ቤት ያለ ምንም ክስና ፍርድ መቆየታቸዉ ይታወቃል። ባለፈዉ ሳምንት ረቡዕ ልደታ በሚገኘዉ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለመጀመርያ ግዜ ቀርበዉ የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ መከሰሳቸዉ ይፋ ሆንዋል። የተከሰሱበት ምክንያትም አቶ ዮናታን በሚያራምዱት የፖለቲካ መንግስት ላይ ተፅኖ ለማሳደር ኅብረተሰቡን አስፈራርተዋል፤ በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ፌስ ቡክን ተጠቅመዉ መንግስት በኦሮሞ ነፃነት ግንባር ተጀመረ የሚለዉን ተቃዎሞ በ«አመፅ እና ብጥብጥ» አስቀጥለዋል በማሉም ተጠቅሶአል።

ይህን የክስ ነጥብ አስመልክቶ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትኔት «የፈጠራ» እና «አስቂቅኝ» ክስ ሲሉ ነዉ የገለፁት። የቀድሞ ባልደረባቸዉን አቶ ዮናታንን ለመጠየቅ ወደ ቅሊንጦ እስር ቤት በማምራት ላይ የነበሩት ኢንጂኔር ይልቃል፤ የክስ ወረቀቱን ማየታቸዉንም እንዲህ ገልፀዋል።

የሕግ ባለሙያና ጠበቃ የሆኑት አቶ ታማም አባቡልጉ በበኩላቸዉ ግለሰቡ መከሰሰ አልነበረበትም ሲሉ ጉዳዩ እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የፀረ ሽብር ሕጉን ስያወጣ ሽብርና ሽብርተኞችን በኢትዮጲያ ዉስጥ በመኖራቸዉ ሳይሆን በጠቃላይ የፖለቲካተቃዉሞን ለማፈን የሚሉት የፖለትካ ምሁር እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፤ የአቶ ዮናታንን ክስ በተመለከተ

በአሜሪካ ሕጋዊ ፍቃድ ይዘዉ ለሚንቀሳቀሱ የሚዲያ ተቋማት ለምን ቃለ-ምልልስ ሰጣችሁ ተብለዉ የሚከሰሱም እንዳሉ ፕሮፌሰር መረራ ተናግረዋል።

ይሄንኑ ጉዳይ በተመለከተ በዶቼ ቬሌ የፌስ-ቡክ ደህረ ገፅ ላይ ተከታታዮች ባስቀመጡት አስተያየት መንግስት እየወሰደ ያለዉ ርምጃ ሃሳብን በነፃነት መግለጽና በሃገሪቱ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ መወያየት ተፅኖ እንዳለዉ ጠቁሞዋል።

መርጋ ዮናስ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic