1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የቀይ ባህር የንግድ መስመር የታወከባቸው ምክንያቶች

ሐሙስ፣ የካቲት 28 2016

አሜሪካና ብሪታኒያ በሁቲዎቹ ላይ በከፈቱት ጥቃት አቅማቸውን እንዳዳከሙትና የማጥቃት ብቃታቸውን ቀንሰናል ቢሉም ሁቲዎቹን እንዳይተኩሱ ሊይደርጉ የንግድ መስመሩን ደህንነትም ሊያስጠብቁ እንዳልቻሉ ነው የሚነገረው።የአሜሪካና ብሪታኒያ ሚሳይሎች የሁቲዎቹን ጥቃት ሙሉ በሙሉ በማስቆም የቀይ ባህርን ደህንነት ማረጋገጥ መቻላቸውን ብዙዎች ይጠራጠራሉ።

https://p.dw.com/p/4dGro
የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል መርከብ በአደን ባህረ ሰላጤ
የዩናይትድ ስቴትስ ባህር ኃይል መርከብ በአደን ባህረ ሰላጤምስል Taylor A. Elberg/ Us Navy/Handout/dpa/picture alliance

የቀይ ባህር የንግድ መስመር የታወከባቸው ምክንያቶች

የየመን ሁቲዎች፤ እስራኤል በፍልስጤም በተለይም ጋዛ ላይ እያካሄደች ያለውን የቦምብ ድብደባ በመቃወም በቀይ ባህር በኩል በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ በከፈቱት ጥቃት ምክንያት ዋናው የእስያ - አውሮፓ የንግድ መተላለፊያ መስመር ተስተጓጉሏል። በአውርፓ ህብረት፤ አሜሪካና እስራኤል አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ሀማስ መስከረም 26 በእስራኤል ሰላማዊ ዘጎች ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተክትሎ፤ እስራኤል በጋዛ በክፈተችው መጠነ ሰፊ ጥቃት እሳክሁን ከ30 ሺ በላይ ሰዎች የተገደሉና ከ70 ሺ በላይ የቆሰሉ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በኢራን ይደገፋሉ የተባሉት የየመን ሁቲዎች  ይህንን የእስራኤልን ጥቃት በመቃወም፤ ከእስያና አፍሪካ በቀይ ባህር አልፈው ስዊዝ ካናልን በማቋረጥ ወደ አውሮፓ በሚሄዱና በሚመለሱ መርካቦች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ነው።  የቀይ ባህር መስመር 12 ከመቶው የአለም ንግድ በተለይም 30 ከመቶ የሚሆነው የአለም የጭነት መርከቦች የሚስተናገዱበትና የሚያልፉበት ሲሆን፤ ባሁኑ ወቅት ግን ይህ መስመር ሙሉ በሙሉ ባይዘጋም ብዝዎቹ መርከቦች አቅጣቻቸውን እንዲቀይሩ እንደተገደዱ ነው የሚነገረው።

የሁቲዎች ጥቃትና የአሜሪክና ብርታኒያ የአጸፋ ጥቃት ዉጤት

ሁቲዎቹ እስካሁን ቢያንስ በአስር የንግድ መርከቦችና የጦር መርከቦች ላይ ጭምር ጥቃት እንደሰነዘሩና አንድ መርከብም እንዳሰመጡ የሚታወቅ ሲሆን፤ በትናትናው እለትም በአንድ የንግድ መርከብ ላይ በስነዘሩት ጥቃት 3 የመርከቡ ሰራቶች እንደሞቱና አራት እንደቆሰሉ ተነግሯል።  ።ምዕራባውያን በተለይም  አሜሪካና ብርታኒያ በአጸፋው  በሁቲዎቹ ላይ በከፈቱት ጥቃት አቅማቸውን እንዳዳከሙትና የማጥቃት ብቃታቸውን እንደቀነሱት ቢያስታውቁም፤ እስካሁን ግን ሁቲዎቹን እንዳይተኩሱ ሊይደርጉ፤ የንግድ መስመሩን ደህንነትም ሊያስጠብቁ እንዳልቻሉ ነው የሚነገረው።

 ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች የታጠቁ የሁቲ ደጋፊዎች
ቀላልና ከባድ የጦር መሳሪያዎች የታጠቁ የሁቲ ደጋፊዎች ምስል Mohammed Hamoud/Anadolu/picture alliance

የአሜሪካና ብርታኒያ ሚሳይሎች የሁቲዎቹን ጥቃት ሙሉ በሙሉ በማስቆም የቀይ ባህርን ደህንነት ማረጋገጥ መቻላቸውን ብዙዎች ይጠራጠራሉ። በኒው ሃቨን ዩንቨርስቲ የወንጀልና ፍትህ መምህር የሆኑት ሚስተር ከርን ግሬይ እንደሚሉት፤ የሁቲን ሚሳይሎችና ድሮኖች በተመሳሳይ ሁኒታ በሚሳይልና ድሮን ማስቆም ኣይቻልም። “ ሁቲዎቹ መሳሪያው እስካላቸው ድረስ በመርከቦች ላይ የሚሰነዝሩትን ጥቃት የሚያቆሙ አይሆንም። በአሜሪካና ብርታኒያ በኩል አቅማቸውን በማዳከም ጥቃት እንዳያደርሱ የተደረጉት ጥረቶች  እስካሁን ውጤት አላስገኙም ወይም ጥቃቱን አላስቆሙም።  በአሁኑ ወቅት እንዴት ወታደሮችን ማሰማራት እንደሚቻል በተለይ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር ንግግር እየተደረገ ቢሆንም ፤ሳዑዲ ግን ዳግም ከሁቲዎቹ ጋር ጦርነት መክፈት የምትፈልግ አይመስልም። ስለዚህ ሌሎች አጋር አገሮችን መፈለግ ወይም የራሳቸውን የአሜሪካና  ብርታኒያ ወታደሮችን ማሰማራት ይኖርባቸዋል” በማለት ይህ ግን ሊሆን እንደማይችል ገልጸዋል።የየመን ሁቲዎች በቀይ ባህር የሚፈጽሙት ጥቃትና ያገኛሉ የሚባሉት ጥቅሞች

የቀይ ባህር መታወክ የጎዳቸው የአፍሪካ አገሮች

በአሁኑ ወቅት በርካታ የመርከብ ኩባንያዎች መርከቦቻቸው  ከእስያ ወደ አውሮፓ ወይም ከአውሮፓ ወደ እስያና ምስራቅ አፍሪካ የሚያደርጓቸውን ጉዞዎች እንዲሰርዙ ወይንም መንገዳቸውን ዙረው በደቡብ አፍሪካ በኩል እንዲያደርጉ እንደተገደዱ ነው የሚታወቀው።  በዚህም በተለይ በኤደን የባህር ሰላጤና የቀይ ባህር  የሚገኙ የጂቡቲ፣  ሳኡዲና ኤርትራ ወደቦች ከፍተኛ ኪሳራ እንደሚደርስባቸው የሚገምት ሲሆን፤  ከሁሉም ግን የስዊዝ ካናል ባለቤቷ ግብጽ ክፉኛ እንደምትጎዳ ነው የሚታወቀው። ግብጽ በዚሁ ሁከት ምክኒያት በስዊዝ ካናል ከሚያልፉ መርከቦች  ታገኝ የነበረውን ለምሳሌ በጥር ወር ብቻ 400 ሚሊዮን ዶላር እንዳጣች ነው መርጃዎች የሚጠቁሙት።

የሁቲዎች ድሮኖችና ራኬቶች ትርዒት በሰንዓ
የሁቲዎች ድሮኖችና ራኬቶች ትርዒት በሰንዓምስል Osamah Yahya/ZUMA Press Wire via picture alliance

የቀይ ባህር መስመር መታወክ ገበያ የፈጠረላቸው ወደቦችና የችግሩ መውጫ መንገድ

በሌላ  በኩል መዳረሻቸውን አውሮፓ አድርገው በደቡብ አፍሪካ በኩል ዙረው የሚጓዙ መርከቦች ለሞዛምቢክ፣ ማዲጋስካር፤ ደቡብ አፍርካ፤ አንጎላና  ናምቢያ ወደቦች  ገበያ እንደፈጠሩላቸው  ነው የሚነገረው። እነዚህ ወደቦች በዚያ በኩል ለሚተላለፉት መርከቦች የነዳጅ መሙሊያ፤ ማረፊያና ልዩ ልዩ አገልግሎትችን ማግኛ በመሆን ያሚያገለግሉ ሲሆን፤ ይህም ለየአገሮቹ ከፍተኛ ዪኢኮኖሚ ጥቅም እያስገኘ እንደሆነ  ነው የሚነገረው።ያም ሆኖ  የፖለቲካ ተንታኙ ሚስተር ሜንዚ ንደህሎቩ  እንደሚሉት እነዚህ አገሮች የሚፈለገውን ያህል ተጠቃሚዎች አልሆኑም። “ እነዚህ አገሮች በዙዎች እንደሚገምቱት ተጠቃሚዎች አልሆኑም። ይህም አጋጣሚውን ለመጠቀም ያሚያስችል መሰረተ ልማት የሌላቸው በመሆኑ ነው” በማለት የአፍሪካ አገሮች  እንደዚህ ላሉ አጋጣሚዎች ተጠቃሚ ለመሆን የወደብ መሰረተ ልማቶችን ማሳደግ የሚገባቸው መሆኑን አስታውቀዋል።

የቀይ ባህር የንግድ መስመር ደህንነት ግን ከአሜሪካና ብርታኒያ የጦር መርከቦች የቀይ ባህር ስምሪት ይልቅ፤ በሀማስና እስራኤል የተኩስ ማቆም ስምምነት ላይ እንደሚወሰን ነው ብዙዎች የሚያምኑትና የሚመክሩትም

 ገበያው ንጉሴ

ኂሩት መለሠ

ነጋሽ መሐመድ