የቀበሌ ካድሬዎች ጫና እና የአርሶ አደሮች ቅሬታ | ኢትዮጵያ | DW | 03.06.2021
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የቀበሌ ካድሬዎች ጫና እና የአርሶ አደሮች ቅሬታ

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ በአንዳንድ ቀበሌዎች የሌላ ፖለቲካ ድርጅት አባላት በመሆናችን ብቻ የቀበሌ ብልፅግና አመራሮች ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ እንዳንወሰድ ከለከሉን ሲሉ አንዳንድ አርሶ አደሮች አመለከቱ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:29

ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ እንዳንወሰድ ከለከሉን

የቀበሌ ካድሬዎች ጫና እና የአርሶ አደሮች ቅሬታ ! በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ በአንዳንድ ቀበሌዎች የሌላ ፖለቲካ ድርጅት አባላት በመሆናችን ብቻ የየቀበሌ ብልፅግና አመራሮች ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ እንዳንወሰድ ከለከሉን ሲሉ አንዳንድ አርሶ አደሮች አመለከቱ፣ የወራዳው አስተዳደር የተባለው ነገር ሐሰት ነው ሲል የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ (አዴኃን) እና ኢዜማ አማራሮችና አባላት ችግሩ በተጨባጭ መፈፀሙን ተናግረዋል፡፡ ከምርጫው መቃረበረ ጋር በተያያዘ ፓርቲዎች የየራሳቸውን ደጋፊ ለማብዛት የተለያዩ የቅስቀሳ ጥረቶችን እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ፓርቲዎች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ህጋዊ በሆነ መልኩ ከሚያደርጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ባለፈ፣ በጫናና ባልተፈቀዱ ቦታዎች ጭምር ቅስቀሳ ሲያደርጉ እንደነበር በተለያዩ መድረኮች ይገለፃል፡፡ ሰሞንንም በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ ኢፋትራ፣ ዳባልና ቆቀር በተባሉ ቀበሌዎች የቀበሌው የብልፅግና ሹማምንት የአዴኃንና የኢዜማ አባል አርሶ አደሮች ምርጥ ዘርና ማዳበሪያ እንዳያገኙ እንደከለከሏቸው አርሶ አደሮች ተናግረዋል፡፡ ኢፍታራ ቀበሌ ትናንት ከ50 እስከ 60 የሚሆኑ አርሶ አደሮች በሌላ የፖለቲካ ድርጅት ስብሰባ፣ ሰልፍና የድርጅቶቹን የምርጫ ምልክትና የመቀስቀሻ አልባሳት ለብሳችኋል በመባላቸው ማዳበሪ መውሰድ እንዳልቻሉ ገልፀዋል፡፡ አንድ የይልማና ዴንሳ ወረዳ ኢዜማ ሥራ አስፈፃሚ አባል ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት የድርጅቱ አባል አርሶ አደሮች የግብርና ግብዓቶችን ለመግዛት ወደ ማዕከላት ሲሄዱ ኢዜማ ይስጣችሁ ይባላሉ፡፡ የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ሰብሳቢና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ይሎች ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ በበኩላቸው ችግሩ ድርጊቱ በእርግጥ በፈፀሙን አመልክተው ጉዳዩን በጋራ መድረኩ እንደሚወያዩበት አመለክተዋል፡፡ የይልማና ዴንሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስናቀ ቢሰማኝ ግን የተባለው ሁሉ ሀሰት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቅነህም ስለተባለው ነገር ሪፖርት እንዳልደረሳቸውና ሁኔታውን እንደሚያጣሩ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል፡፡ 
ዓለምነው መኮንን
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች