የሾንኮራ አገዳ መሬት ውዝግብ | ኢትዮጵያ | DW | 09.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሾንኮራ አገዳ መሬት ውዝግብ

በጥቅምት ወር 2009 ዓ/ም በኦሮሚያ ክልል በተካሄደው ተቃዉሞ በተለያዩ ከተሞች የእርሻ ቦታዎችና ፋብሪካዎች መቃጠላቸዉ ሲዘገብ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:20

የመሬት ግጭት 

የየአካባቢው ነዋሪዎች በተለይ የእርሻ መሬቶች ላይ የደረሱት የቃጠሎዎቹ መንስኤ በልማት ስም መሬት ከገበሬዎች ያለ በቂ ካሳ መወሰዱ መሆኑን ይገልፃሉ። በተቃዉሞዉ ወቅት ቃጠሉ ከደረሰባቸው መካከል የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካን ለመመገብ የተተከሉት የሾንኮራ አገዳ እርሻዎች ይገኙበታል። የሾንኮራ ተክሎቹ በምስራቅ ሸዋ ዞን በአዳማና በቦሰት ወረዳዎች እንድሁም በአርስ ዞን ዉስጥ ደግሞ ዶዶታ ወረዳ ዉስጥ እንደምገኝ የፋብሪካዉ ስራ አስኪያጅ አቶ ቱሉ ለማ ጠቅሰው በአከባቢዉ መንግስት በኒልዮኖች የሚቆጠሩ ገንዘቦችን አፍስሶ የመስኖ መሰረተ ልማት እንደሰራ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል።

የ25 ዓመት ወጣት የሆነዉ ይህ የአዳማ ነዋሪ የሾንኮራ እርሻዉ የተቃጠለዉ መሬቱ ከገበሬዉ በጉለበት ስለተወሰደበት ነዉ ይላል።

ይሁን እንጅ የፋብርካዉ ስራ አስካያጅ አቶ ቱሉ ከገበሬዉ «የተወሰደ መሬትም የለም፣ የሚከፈልም ካሳ የለም፣ አሁንም መሬቱ የገበሬዉ ነዉ፣ ግብርም እየከፈለበት ያለዉ ገበሬዉ ነዉ» ይላሉ። ይልቁንስ አከባብዉ ዝናብ አጠር አከባቢ ስለሆነ አርሶ አደሩ ራሱ በመስኖ ቢያለማው የበለጠ ተጠቃሚ ይሆናል የሚል ህሳቤ ነበረ ይላሉ። በሶስቱም ወረዳዎች 32 የገበሬ ማሃብራት እንዳሉና እነዚህ ማህበራትም አንድ የሾንኮራ አገዳ አምራቾች ህብረት ስራ ማህበር እንዳላቸው ስራ አስኪያጁ ይናገራሉ።

ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልኩ ነዉ፣ ገበሬዎቹንም ሆነ ልጆቻቸዉን አነጋግሬያለሁ የሚሉት እኝህ የአዳማ ነዋሪ ግን ስራ አስኪያጁ አለ ያሉት ስምምነት ቢኖርም ገበሪዎቹ የሚያገኙት ገቢ ግን  በጣም ጥንሽ ነዉ ይላሉ።

ይህ የተቃጠለ የሾንኮራ እርሻ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል ለሚለዉ አቶ ቱሉ ሲመሊሱ፣ አርሶ አደሩ ራሱ ዳግም ወደ ተከላ እንደገባና ወደ ፊትም ለሚፈጠሩት ችግሮች ፋብሪካዉና የአምራቾቹ ማህበር እየተገናኙ አብረው ይሰራሉ ሲሉ ተናግረዋል ። የአከባቢዉ ነዋሪዎች ደግሞ አርሶ አደሩ ዳግም ተከላው ላይ የተሳተፈው ተገዶ እንጅ ወዶ አይደለም ይላሉ።

የወንጅ ሾዋ ስኳር ፋብርካ የሾንኮራ አገዳ ፍላጎቱ በመጨመሩ የእርሻ መሬቱን ወደ 6000 ሄክታር ለማሳደግ ማቀዱ ተዘግቦ ነበር። ከዚህም ዉስጥ 75 በመቶዉ በገበሬዎች እንደሚለማም ተጠቅሷል። የሾንኮራ አገዳዉ ቆረጣ ሲደርስም አንድ ኩንታል በ50 ብር ለመቀበል እቅድ እንደነበረዉ ተዘግቧል።

መርጋ ዮናስ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic