የሽንገን ስምምነትና አዲሱ የማሻሻያ ሰነድ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 06.05.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሽንገን ስምምነትና አዲሱ የማሻሻያ ሰነድ

የሸንገን ስምምነት ላይ የማሻሻያ ሀሳብ ቀርቧል። በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት መሀል በሸንገን ዙሪያ የተፈጠረውን ውዝግብ ለመፍታት ነው ተብሏል።

default

የአውሮፓ ኮሚሽን ወደ ህብረቱ የሚፈልሱና ጥገኝነት የሚጠይቁ ሰዎችን፤ ወጥ በሆነ መንገድ ለማስኬድ ያስችላል ያለውን የአሰራር ስልትና እ.ኤ.አ ከ1995 ወዲህ በህብረቱ አባል ሀገራት መካከል የነበረውን የድንበር ቁጥጥር ያስወገደውን የሸንገን ስምምነት በሚመለከት ያዘጋጀውን የማሻሻያ ሀሳብ ሰነድ ይፋ አድርጓል። ይህ የማሻሻያ ሰነድ የተዘጋጀው ሰሜን አፍሪካ የተቀጣጠለው አብዮት ያስከተለው የህዝብ ፍልሰትን ለመቆጣጠርና በአባል ሀገራት መካከል በዚሁ በሸንገን ስምምነት ላይ የተፈጠረውን አለመግባባት ከግምት በማስገባት እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። ከብራስልስ ገበያው ንጉሴ የላከው ዘገባ ቀጥሎ ይቀርባል።

ገበያው ንጉሴ

መሳይ መኮንን

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic