የሽታይንብሩክ አስተያየትና ትችቱ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 03.01.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

የሽታይንብሩክ አስተያየትና ትችቱ

ሽታይን ብሩክ የጀርመን መራሄ መንግሥት ደሞዝ መሻሻል አለበት ፣ በመጪው ምርጫ የሚፎካከሯቸው የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲዋ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተዋቂ ፖለቲከኛ ለመሆን የበቁት ሴት በመሆናቸው ነው ማለታቸው በራሳቸው ፓርቲ አባላት ጭምር አስተችቷቸዋል ።

አንጋፋው የጀርመን ሶሻል ዲሞክራቶች ፓርቲ ፖለቲከኛና የመጪው የጀርመን አጠቃላይ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ፔር ሽታይን ብሩክ ሰሞኑን የሰጡት አስተያየት እዚህ ጀርመን እያነጋገረ ነው ። ሽታይንብሩክ የጀርመን መራሄ መንግሥት ደሞዝ መሻሻል አለበት ፣ በመጪው ምርጫ የሚፎካከሯቸው የክርስቲያን ዲሞክራት ህብረት ፓርቲዋ እጩ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ተዋቂ ፖለቲከኛ ለመሆን የበቁት ሴት በመሆናቸው ነው ማለታቸው በራሳቸው ፓርቲ አባላት ጭምር አስተችቷቸዋል ። የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ሽታይንብሩክ ስለሰጡት አወዛጋቢ አስተያየትና አስተያየቱ ስለሚያሳድርባቸው ተፅዕኖ የበርሊኑን ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን በስልክ ጠይቀናል ።

ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic