የሽታይንማየር የኢትዮጵያ ጉብኝት እድምታ | ኢትዮጵያ | DW | 30.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሽታይንማየር የኢትዮጵያ ጉብኝት እድምታ

የጀርመኑ ግዙፍ የመኪና አምራች ድርጅት ፎልክስ ቫገን መገጣጠሚያ በኢትዮጵያ ለማቋቋምና ግብአቶችን ለማምረት የሚያስችለው ስምምነት ከፍተኛ ቁጥር ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ተሸከርካሪ ማግኘት የሚችልበትን እድል የሚያሰፋ ሰፊ የኢንቨስትመንት ተጠቃሚነትንና የስራ አድልን ከቴክኖሎጅ ሽግግር ጋር ይዞ እንደሚመጣ DW ያነጋገራቸው ባለሙያዎች አስረድተዋል፡፡

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:18

የሽታይንማየር የኢትዮጵያ ጉብኝት አንድምታ

የጀርመኑ ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታየንማየር በኢትዮጵያ ያደረጉት ጉብኝት የሁለቱን ሃገሮች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከወዲሁ ትልቅ ምልክት የታየበት መሆኑን DW ያነጋገራቸው የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የህግ ምሁር እና ጋዜጠኛ ተናገሩ ፡፡ ግንኙነቱ በሃገር መሪ ደረጃ መደረጉ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ክብደት እንደሚሰጠው እና በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ቀጥተኛ መረጃ እንዲያገኙ እድል ያለው መሆኑን የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ዘመዴ ነህ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል ጀርመን በአፍሪቃም ይሁን በኢትዮጵያ ያላትን ዝቅተኛ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ እድል የሚፈጥር እንደሚሆንም አብራርተዋል፡፡ ጀርመን ለመላው አፍሪቃም ይሁን ለኢትዮጵያ ቀና አመለካከት ያላት ሃገር ናት የሚለው ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ይህ የፕሬዝዳንቱ የኢትዮጵያ ጉብኝት ቀና አመለካከታቸውን ወደ ተግባር የሚለውጡበት መልካም እድል እንደሆነና በጅምር ደረጃ የሚታይ ጥሩ እርምጃ መሆኑን አውስቷል፡፡ የጀርመኑን ግዙፍ የመኪና አምራች ድርጅት ፎልክስ ቫገን መገጣጠሚያ በኢትዮጵያ ለማቋቋምና ግብአቶችን ለማምረት በሁለቱ ሃገራት መካከል የተደረገው ስምምነት ከፍተኛ ቁጥር ላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ተሸከርካሪ ማግኘት የሚችልበትን እድል እንደሚያሰፋ ፡ ሰፊ የኢንቨስትመንት ተጠቃሚነትንና የስራ አድልን ከቴክኖሎጅ ሽግግር ጋር ይዞ እንደሚመጣ ፡ ለጀርመንም ከፍተኛ የገበያ አማራጭ እንደሚፈጥር DW ያነጋገራቸው ባለሙያዎች አስረድተዋል፡፡ ሰሎሞን ሙጩ ከአዲስ አበባ ተጨማሪ ዘገባ አለው።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic