የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉ ፀረ- ሽብር ርምጃ | እንወያይ | DW | 20.12.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

እንወያይ

የሽብር ጥቃት ሥጋትና ዓለም አቀፉ ፀረ- ሽብር ርምጃ

የዛሬ 14 ዓመት በዬኤስ አሜሪካ ከደረሰዉ የአሸባሪዎች ጥቃት ወዲህ ዓለም ከቀን ወደ ቀን በሽብር ሥጋት ዉስጥ ትገኛለች። ይሁንና የሽብሩን ጥቃት ለመከላከል የሚወሰደዉ ፀረ-ሽብር ርምጃ ሙሉ በሙሉ ዉጤታማ አለመሆኑ ነዉ የሚታየዉና የሚነገረዉ። ጥቃትና የአፀፋ ጥቃቱ ቀጥሎ፤ አሸባሪዎቹም ሳይጠፉ ስማቸዉን በመቀያየር የፀረ ሽብሩ ዘመቻም መቋጫ ሳያገኝ እንደዉም ፅንፈኝነት እየገነነ አገር እየወደመ፤ ሽብሩ አሜሪካ፤ አፍሪቃ፤ መካከለኛዉ ምስራቅ ብሎ መኃል አዉሮጳ ደርሶአል። ዉይይቱ በቅርቡ የኢትዮጵያ መንግሥት የአዲስ አበባና የኦሮምያ ልዩ ዞን የተቀናጀ እቅድን በመቃወም በተፈጠረው ብጥብጥ እጃቸው አለበት የተባሉትና በአሸባሪነት በተፈረጁት ላይ የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ ማስጠንቀቁን በተመለከተ አስተያየትም ጠይቀናል። ሙሉዉን ዉይይት የድምፅ ማድመጫዉን ማዕቀፍ በመጫን ይከታተሉ።

Audios and videos on the topic