የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ | ኢትዮጵያ | DW | 17.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

የሽብር ጥቃት ማስጠንቀቂያ

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ከሽብርተኞች አዲስ አበባ ከተማ ዉስጥ ጥቃት እናደርሳለን የሚል ማስጠንቀቂያ እንደደረሰዉ በያዝነዉ ሳምንት መጀመሪያ ቀናት ላይ አስታዉቋል።

ኤምባሲዉ በጽሑፍ ባወጣዉ መግለጫ ዜጎቹ በተለይም በቦሌ አካባቢ የዉጭ ዲፕሎማቶች በሚያዘወትሯቸዉ ስፍራዎች፤ ሕዝብ በሚበዛባቸዉ፤ በሆቴልና ምግብ ቤቶች ከመገኘት እንዲታቀቡ አሳስቧል። እንደመግለጫዉ የአምልኮ ስፍራዎችም የጥቃቱ ኢላማዎች ሊሆኑ እንደቸሚችሉ ተገምቷል። የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣን በበኩላቸዉ አሸባብ ጥቃት የመጣል ፍላጎት ቢኖረዉ እንኳ ተግባራዊ የመሆኑ ነገር ተስፋ እንደሌለዉ ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። የአሜሪካ ኤምባሲዉ ያወጣዉን መግለጫ መሠረት በማድረግ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይን ያነጋገረዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ከአዲስ አበባ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic