የሽመና ባለሞያዉ ወጣት ስኬቶች  | ባህል | DW | 28.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

የሽመና ባለሞያዉ ወጣት ስኬቶች 

አለባቸው ምህረት የሽመና ሥራን የጀመረዉ በ 600 ብር ነዉ። ወጣቱ የሽመና ዉጤት አፍቃሪ ያቋቋመዉ የሽመና ድርጅት ዛሬ የ 35 ሚሊዮን ባለቤት መሆኑን ይናገራል። ድርጅቱ ወደ 640 ለሚሆኑ ዜጎችም የሥራ እድልን ፈጥሮአል። ድርጅቱ የሚያመርታቸዉ የሽመና ዉጤቶች በሃገር ቤት ብቻ ሳይሆን በተለያዩ የዉጭ ሃገራት በገፍ ይሸጣሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 11:43

ቁጠባን ባህል ማድረግ ያስፈልጋል


አለባቸው ምህረት ትውልዱና እድገቱ ጎንደር ነው፡፡ በ2005 ዓም የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን በከፍተኛ ነጥብ ቢያጠናቅቅም ዝንባሌውና ፍላጎቱ አሸንፎት ወዲያውኑ የተሰማራው በሸማ ስራ ነበር፡፡ በ600 ብር መነሻ ካፒታል ጎንደር አካባቢ ሥራውን የጀመረው አለባቸው በአካባቢው የሸማ ስራ በአብዛኛው ህብረተሰብ ዘንድ እንደዝቅተኛ የስራ መስክ የሚታይና የሚናቅ ስለነበር ከቤተሰቡ ጀምሮ በጓደኛና ዘመድ መገለሉን ይናገራል፡፡


ጫናው የበረታበት አለባቸው ታዲያ አካባቢውን መልቀቅ አማራጭ መሆኑን በማመን  የትውልድ ቀየውን ትቶ ወደባሕር ዳር እንደመጣ ይናገራል፡፡ ባሕርዳር ሥራ ቢጀምርም የቦታና የካፒታል እጥረት አጋጥሞት እንደነበርና ሥደትን እንደ ሌላ አማራጭ ወስዶ ወደ ጃፓን አገር ለመሄድ ወስኖ ከጨረሰ በኋላ አንድ የወቅቱ የብአዴን አመራር ትጋቱንና የስራ ፍላጎቱን በማየት በአነስተኛና ጥቃቅን እንዲደራጅና የብድርና የቦታ ጥያቄው መልስ እንዲያገኝ በማድረጉ ስራውን ባግባቡ እንዲሰራ በር እንደከፈተለት ተናግሯል፡፡
የተፈተሉ የሽመና ግብዓቶችን ከአርባ ምንጭና ከአክሱም ያስመጣ እንደነበር የሚናገረው አለባቸው የቦታና የብድር አገልግሎት ካገኘ በኋላ የአካባቢውን እናቶች በማደራጀት በጥጥ ፈትል ስራ እንዳሰማራቸው አመልክቷል፡፡
ሥራው እየሰፋ ሲሄድና የባህላዊ ልብስ ፍላጎት እያደገ ሲመጣ ከአበዳሪ ተtቋማት ብድር እየወሰደ ስራውን ዘመናዊ ማሽኖችን በማስገባትና የሰው ኃይሉን፣ የካፒታል አቅሙንና የገበያ ተደራሽነቱን በከፍተኛ ሁኔታ ማስፋቱንና ማሳደጉን አለባቸው ያብራራል፡፡በሰራተኞች መካከል ስራ ተነሳሽነትና ፉክክር እንዲኖር በየመቱ ድርጅቱ በሚያወጠው መስፈርት መሰረት ሽልማቶች ይደረጋሉ ሰራተኞች እንዲቆትቡም ግፊት ደረጋል ብሏል፡፡

 
ከዚህ በተረፈም ብቁ ሰራተኞች ራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ እንደሚድርግ ነው የ30 ዐማቱ ወጣት የሚናገረው፡፡የጠየቁት ተጨማሪ የመስሪያ ቦታ በከተማ መስተዳደሩ ተቀባይነት በማግኘቱም የሰራተኛውን ቁጥር ወደ 1000 ለማሳደግ ማቀዱንም አለባቸው አስረድቷል፡፡ያኔ ወደ ስራው ሲገባ ይቃወሙት ነበሩ ጓደኖቹ ዛሬ የያዙትን የመንግስት ስራ እየተው “የባህል ልብስ ድርጅት” ተቀጥረው እየሰሩ እንደሆነ ተናግሯል፡፡ ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ! 

አለምነዉ መኮንን
አዜብ ታደሰ 

Audios and videos on the topic