የሼክ መሐመድ አል-አሙዲ ቤተሰቦች አልታሰሩም | ዓለም | DW | 02.02.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሼክ መሐመድ አል-አሙዲ ቤተሰቦች አልታሰሩም

ሚድል ኢስት ሞኒተር የተባለው ድረ-ገፅ እንደዘገበው የሼክ ሙሐመድ አል-አሙዲ ቤተሰቦች ለእስር የተዳረጉት የ71 አመቱ ባለወረት ገንዘብ እና ንብረታቸውን ለማስረከብ አሻፈረኝ በማለታቸው ነው። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ስለሺ ሽብሩ እንደሚለው ግን መረጃው የተሳሳተ ነው።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09

የሼክ መሐመድ አል-አሙዲ ቤተሰቦች ጉዳይ

በሳዑዲ አረቢያ መንግሥት የጸረ-ሙስና ዘመቻ በእስር ላይ የሚገኙት ሼክ ሙሐመድ አል-አሙዲ ቤተሰቦች ታስረዋል የሚል ወሬ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ገደማ ተሰምቶ ነበር። ሚድል ኢስት ሞኒተር የተባለው ድረ-ገፅ እንደዘገበው የሼክ ሙሐመድ አል-አሙዲ ቤተሰቦች ለእስር የተዳረጉት የ71 አመቱ ባለወረት ገንዘብ እና ንብረታቸውን ለማስረከብ አሻፈረኝ በማለታቸው ነው። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የዶይቼ ቬለ ወኪል ስለሺ ሽብሩ እንደሚለው ግን መረጃው የተሳሳተ ነው። ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ የሚገኘው ስለሺ ከአስራ አንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚገመት ሐብት ባለቤት የሆኑት አል-አሙዲ ቀድሞ ከነበሩበት ቅንጡ ሆቴል መዘዋወራቸውን ተናግሯል። ሳዑዲ አረቢያ በሙስና የጠረጠረቻቸውን ልዑላን እና የናጠጡ ባለወረቶች ለወራት ከተካሔደ ምስጢራዊ ድርድር በኋላ መፍታት ጀምራለች።  
ስለሺ ሽብሩ
እሸቴ በቀለ
ኂሩት መለሰ 
 

Audios and videos on the topic