የሼል ኩባንያ ችሎት በደን ኻግ | አፍሪቃ | DW | 11.10.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሼል ኩባንያ ችሎት በደን ኻግ

የሼል ኩባንያ በኒዤር ዴልታ በተፈጠረው የአካባቢ ብክለት በደን ኻግ በሚገኘው ፍ/ቤት ተከሶ ዛሬ ቀረበ። ከሳሾቹም አራት የናይጀርያ ገበሬዎች ናቸው። በአውሮፓ፣ ዘይት ወደ አከባቢ ተለቆ የባህር ዳርቻን ሲያቆሽሽ ፣ በርግጠኝነት ህግ ፊት ቀርቦ ውሳኔ ማግኘት የሚገባው ጉዳይ ይሆናል።

Jan 26, 2005; Ogoni, Rivers State, NIGERIA; K-Dere Community; Farmer Bakpa Birabil stands in front of two leaking oil wells on his farm, which has been owned by his family for centuries. The oil well (on his property) has been leaking for the past year without attention from Shell. Multinational oil companies, including Shell Oil (the biggest oil company in the Niger River Delta) have drawn attention because of poor business practices and inability to work with local communities. Tension between Nigerians living in the area, the Nigerian government and the oil production industry has made the Niger River Delta one of the most dangerous and volatile places on earth to conduct business. Mandatory Credit: Photo by Mark Allen Johnson/ZPress +++(c) dpa - Report+++

Ölquelle in Nigeria

በአውሮፓ፣ ዘይት ወደ አከባቢ ተለቆ የባህር ዳርቻን ሲያቆሽሽ ፣ በርግጠኝነት ህግ ፊት ቀርቦ ውሳኔ በኒጀር ዴልታስ አከባቢውን በሙሉ ያበላሸ የዘይት ብከላ እንዴት ይታይ ይሆን? ለዚህ በናይጄርያ ተፈጥሯል ለተባለው ያከባቢ ብክለት ተጠያቂ ነው የሚል ክስ የቀረበበት የ ሼል ኩባኒያው ችሎት ዛሬ በኔዘርላንድ ፍርድ ቤት ቀርቦ መልስ ሰጥቷል።

በኒጄር ዴልታ የሚገኙ ወንዞችና ሓይቆች ከዚህ በፊት በአከባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮችና በአሣ ምርት የሚተዳደሩ ሰዎች የህይወት ምንጭ ነበሩ። ዛሬ ግን ቦታው በነዳጅ ዘይት ዝቃጭ ተበክሏል። ሃምሳ ዓመት ያስቆጠረው ይህ የነዳጅ ዘይት ምርት ባስከተለው መዘዝ ምክንያት፣ አከባቢውን መልሶ የማጽዳቱ ሥራ 30 ዓመት እንደሚወስድና እስከ አንድ ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያስወጣ፣ ከዓመት በፊት በተባበሩት መንግስታት የተሰራ አንድ ጥናት ያመለክታል። ለዚህ የአከባቢ ብከላ ኃላፊነቱን የሚወስድ ማነው?

This undated photo shows a Shell Oil rig in the Niger Delta, Nigeria. Nigeria's latest hostage crisis came to a peaceful end Sunday, June 4, 2006, as six Britons, one American and one Canadian held captive for two days were released unharmed, looking tired, but in good health. A group of unidentified militants from southeastern Bayesla state who were demanding jobs and money kidnapped the expatriates Friday from an offshore oil platform operated by Dolphin Drilling Ltd. (AP Photo/Shell Oil)

Nigeria Ölplattform vor der Küste

«ሁለት የአሰራር መስፈርት ያላቸው የሚመስሉ እንደ ሼል ያሉ ድርጅቶች በአውሮፓና እንደ ናይጄሪያ ባሉ ሀገራት፣ የሚከተሉት አሰራር እጅግ የተለያየ ነው። አንድ የነዳጅ ዘይት ኩባንያ የእርሻ መሬትን በዘይት ዝቃጭ ማቆሸሽ እንዲቆም እርምጃ ሳይወስድ የሚያልፍበት ሁኔታ አውሮፓ ውስጥ ከቶውኑ አይታሰብም። ግን ናይጄሪያ ውስጥ ይህን ማድረግ ችሎዋል። በዚህ መልኩ ነው አንድ ኩባኒያ ያከባቢ መጠበቂያ መስፈርቶችን ችላ ማለት የሚጀምረው።»

በዚህ ምክንያት ነው ሚልዬ ዴፎንሲ በተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የሚሰሩት ጊርት ሪትሴማ፣ ከአራት የናይጄሪያ አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በሼል ኩባኒያ ላይ ክስ የመሰረቱት። ጥያቄያቸውም፣ አከባቢውውን የሚበክል የነዳጅ ዘይት መንጠባጠብን ለማስቆም አዲስ ማስተላለፊያ ቧንቧዎች እንዲሰሩና አከባበው በተገቢው እንዲጸዳ፣ እንዲሁም መታዳደሪያ ስራቸውን በነዳጅ ዘይቱ ምክንያት ላጡ ያከባቢው አርሶ አደሮችና አሳ አጥማጆች ካሳ እንዲከፈል ነው።

አንድ ኩባንያ በሌላ ሀገር ውስጥ ለፈጸመው ጥፋት ፍርድ ቤት መቅረቡ በአውሮፓ የታዋቀ አይደለም። የህጉ ጉዳይ ብዙውን ጊዜ ግልጽ አይደለም። የአውሮጳ ፍርድ ቤት ለመሆኑ አውሮጳ ውስጥ ያልተከሰተውን የክስ ጉዳይ ለመመልከት ለመሆኑ ኃላፊነቱ አለው? እንዲህ አይነት የፍርድ ሂደት ከፍ ያለ ወጪ የሚያስወጣ ብቻ ሳይሆን፣ ሌሎች ብዙ እንቅፋቶች አሉት ይላሉ በጀርመኑ ኡትሬችት ዩኒቨርስቲ የህግ ባለሙያዋ ሊስቤት ኤኔኪንግ፣

Durch Öl verschmutzter See im Ogoniland, Niger-Delta. Copyright: Mazen Saggar, UNEP

Verschmutzter See im Ogoniland Niger-Delta

«አብዛኞቹ ማስረጃዎች ያሉት በከሳሹ ሳይሆን በተከሳሹ ኩባኒያ እጅ ነው። ለምን ነዳጅ ዘይቱ ተንጠባጠበ?፣ የነዳጅ ዘይት መተላለፍያ ቧምቧዎች በምን ያክል ጊዜ ውስጥ እድሳት ይደረግላቸዋል? የተበላሹት በጥንቃቄ ጉድለት ነው ወይስ ሆን ተብሎ ነው? ሼል፣ ነዳጅ ዘይቱ ወደ አከባቢው ከመፍሰሱ በኋላ ዬትኞቹን እርምጃዎች ወስዷል? የሮያል ደች ሼል ኩባኒያ በናይጄሪያ ስለሚገኘው የዘይት መተላለፍያ ቧምቧ አያያዝ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ አለው ለሚሉ ጥያቄዎች ማስረጃ ያስፈልጋል።»

ሼል እነኚን ጥያቄዎች በፍርድ ሂደቱ ውስጥ መመለስ ይገበዋል። ኩባኒያው በኔዘርላንድ እየተካሄደ ያለውን የህግ ሂደት ወደ ናይጄሪያ ፍርድ ቤት እንዲዞርለት ሞክሯል። <<ተጠያቂው በናይጄሪያ የሚገኘው የሼል እህት ኩባኒያ ነው>> የሚለውን የሼል ክርክር፣ የሄጉ ፍርድ ቤት ዳኛ ውድቅ አድርገዋል።

«በኔዘርላንድስ በሚገኘው የሮያል ደች ኩባኒያ ብቻ ሳይሆን፣ በናይጄሪያ የሼል እህት ኩባኒያም ለጉዳዩ ተጠያቂዎች መሆናቸውን ፍርድ ቤቱ አውጇል። ይህ ለሌሎቹም እንደ ምሳሌ ሊያገለግል የሚችል የህግ ጉዳይ ነው። አሁን በኔዘርላንድስ ፍርድቤት ግዙፍ ዓለም አቀፍ ኩባኒውያን ሲከሰሱ እናት ኩባኒያ ብቻ ላይ ሳይሆን በሌላ ሀገር በሚገኝ እህት ኩባኒያ ላይም ክስ መመስረት ይቻላል።»

በአውሮፓ እንዲህ አይነት ክስ ከዚህ በፊት የታየው በአንድ የለንዶን ፍርድ ቤት ነበር። ብዙን ጊዜ ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባኒያዎችን በተመለከተ የሚነሱ ክሶች የሚሰሙት ከወደ አሜሪካ ነው።

ዛሬ በተካሄደው የሄግ ፍርድ ቤት ውሎ በናይጄሪያ በዘይት ማስተላለፍያ ቧምቧዎች ላይ የደረሰ ብልሽት ሆን ተብሎ የተደረገ የማበላሸት እርምጃና በስርቆት ምክንያት ነው ሲል ሼል ኩባኒያ ተከራክሯል። የከሳሾቹ ጠበቃ ግን ቧምቧዎቹ ከጊዜ ርዝመት የተነሳ መዛጋቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። የፍርድ ቤቱ የመጨረሻ ውሳኔ በያዝነው የፈረንጆች ዓመት መጨረሻ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

ቬራ ከርን

ገመቹ በቀለ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 11.10.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16OWv
 • ቀን 11.10.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/16OWv