′የሻገተ ዜና′ እና ሮቤል ተመስገን | ባህል | DW | 09.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

'የሻገተ ዜና' እና ሮቤል ተመስገን

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት መምህር የሆነው ወጣት ሮቤል ተመስገን በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እና ጸኃፍትን የህይወት ውጣ ውረድ 'የሻገተ ዜና' የተሰኘ ሥራ በመስራት ላይ ይገኛል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:33

'የሻገተ ዜና' እና ሮቤል ተመስገን

ከዚህ ቀደም በለንደን አድባር የተሰኘ ሥራውን ለእይታ ያቀረበው ሮቤል በኢትዮጵያ መንግስት ክስ ተመስርቶባቸው የተዘጉ ጋዜጦች ላይ ትኩረት አድርጓል። ሮቤል ተመስገን በርሊን ከተማ በሚገኘው አካዳሚያ ዴር ኩንስተ የጥበብ ማዕከል 'የሻገተ ዜና' የሚል ርዕስ የሰጠውን የጥበብ ስራ በመሥራት ላይ ይኛል። ሮቤል በማዕከሉ የሚቆየው ለሶስት ወራት ብቻ ሲሆን በሥራው ሰዓሊው ከዚህ ቀደም ከለመደው አሰራር ወጣ በማለት ራሱን ለመፈተሽ የጀመረው ነው።ሮቤል ባለፉት ዓመታት የታዘበውን የጋዜጠኞች፤ እና ጸሃፍት እስር እና እንግልት በተለየ አተያይ ለማቅረብ ደፋ ቀና እያለ ነው።
ደሴ ተወልዶ ያደገው ሮቤል ተመስገን መጀመሪያ ከስዕል ጋር የተዋወቀው በወንድሙ የሥዕል ስቱዲዮ ወንድሙ እን የወንድሙ ጓደኞች በሚሰሯቸው ሥዕሎች ነበር። በወንድሙ የሥዕል ስቱዲዮ እጁን ያፍታታው ወጣት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው አለ የሥነ-ጥበብ ትምህርት ቤት ተምሯል። ወጣቱ እንደ ሥነ-ጥበብ ባለሙያ እና ኃፊነት እንደሚሰማው ሰው ይህን ሥራ ለመስራት መነሳቱን ይናገራል።
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic