የሺ ጋብቻ | ኢትዮጵያ | DW | 21.11.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሺ ጋብቻ

ሠርግና ሞት አንድ ነዉ የሚለዉ የቆየ ብሂል፤ ሁለቱ አጋጣሚዎች አንድን ሰዉ አንዴ የሚያጋጥሙ መሆናቸዉን ማመላከቻ ከመሆን አልፎ፤ የደመቀ ድግስን ጠቋሚ ነዉ። በዚህ የሚመሩ ታዲያ ተበድረዉ ተለቅተዉ ሠርግ ድል ባለ ድግስ ያሳልፋሉ።

ይህ ግን የሚታየዉ ሀገር ዉስጥ ብቻ እንዳይመስልዎ፤ ከባህር ማዶ ተሻግሮ በሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ ዘንድም ነብር ዥንጉርጉርነቱን ኢትዮጵያዊ መልኩን እንዲሉ፤ በየሀገሩ የሚያጋጥም ነዉ። በተቃራኒዉ በትዳር ሊጣመሩ ወደዉ ይኸዉ ድል ያለ ድግስ እንቅፋት እየሆነባቸዉ ሳይወዱ በግድ ቀናት እንደሚጉዱባቸዉ ሲናገሩ ይደመጣል። ከወጪ አንፃር ሠርግ መደገስ ሳይሳካላቸዉ ለሚቆዩ ወገኖች ደግሞ በህብረት የመሠረጉ ስልት ኢትዮጵያ ዉስጥ መጀመሩ ጥቂት ለማይባሉት እፎይታ መሆኑ ይታያል። ይህ ስልት ዓመታት አስቆጥሯል፤ ባሳለፍነዉ ሳምንት ማለቂያም እንዲሁ ሺዎች የሺ ጋብቻ ተብሎላቸዉ ሶስት ጉልቻቸዉን አሃዱ ብለዉ ጀምረዋል። በዚህ ድግስ ከተጣመሩት አንዳንዶቹን አነጋግሮ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ተከታዩን ዘገባ አድርሶናል።

ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic