የሺ ጂን ፒን የሩስያ ጉብኝት | ዓለም | DW | 22.03.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሺ ጂን ፒን የሩስያ ጉብኝት

የቻይናና የሩስያ የንግድ ግንኙነት ባለፉት 2 አመታት በ 40 በመቶ አድጓል ። ሁለቱ አገሮች የንግድና ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠንናከር አልመዋል ። ይህን የሚያደርጉትም አሜሪካን ፊቷን ወደ እስያ በመመለሷ ነው ።

አዲስ ፕሬዝዳንት ሥልጣን ሲይዝ መላው አለም የመጀመሪያዎቹን እርምጃዎቹን በመከታተል የወደፊቱ የፖለቲካ አቅጣጫው ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገመት ይሞክራል ። ለቻይናው ፕሬዝዳንት የተሰጠው ግምትም ከዚህ የተለየ አይደለም ። የአዲሱየቻይና ፕሬዝዳንት የሺን ጂን ፒንየመጀመሪያው እንግዳ የአሜሪካን የገንዘብ ሚኒስትር ጃክ ሊው ነበሩ ። ቻይና ካላት የተትረፈረፈ ገቢዋ ለአሜሪካ  መንግሥት ብድር በመስጠት የአሜሪካንን መንግሥት የሥራ እንቅስቃሴ እንዳይተጓጎል አድርጋለች ። ፕሬዝዳንት ሺን ጂን ፒን መጀመሪያ የጎበኙት ሃገር ደግሞ ሩስያ ናት ።  የሁለቱ ጎረቤት ሃገሮች የቅርብ ጊዜ የግንኙነት ታሪክ እንደ ቀድሞው ቀጥሏል ሊባል የሚችል አይነት አይደለም ። በቻይና በኩል ፣ ሩስያ ከኮምኒስቷ ሶቭየት ህብረት በፊት የመጀመሪያዋ ተምሳሌት በኋላም ጠላት ሆና የምትታይ ሃገር ነበረች። በመጨረሻም ደግሞ አጋር ሆናለች ።

China Xi Jinping in Moskau 22.03.2013

ሺን በሞስኮ

እጎአበ1950ዎቹሩስያወደኮምኒስቷአገርቻይናበሺህዎችየሚቆጠሩጠበብቶቿንለእርዳታልካነበር።ከዚያም  የሁለቱሃገሮችየርዕዮተዓለምልዩነቶችእየሰፉሄደውበ1960 ዎቹ መጨረሻ በጋራ ድንበራቸው ላይ እስከመታኮስ ደርሰውነበር። በመካከሉ ደግሞ ሁለቱም ወገኖች ስልታዊ አጋር ምሆነው ነበር። ከቱቢንገን ዩኒቨርስቲ ጉንተር ሹበርት ይህን ጉድኝት በተለይ ምዕራባውያኑን ለመቃረን ታስቦ የተመሰረተ ጉድኝት ይሉታል ። የሺን ዢን ፒንግ የሩስያ ጉብኝትም ሃገራቸው ከምዕራቡ አለም በተጨማሪ ወደ ሌላው ክፍለ አለምም እንደምታተኩር እንደ አርማ የሚታይ ጠቋሚ ምልክት ነው ይላሉ ።«እርግጥ  ቻይና ለሩሲያ ጠቃሚና ተፈላጊ ሀገር ናት፤ ለቻይና የኅይል ምንጭ ፍላጎት፣  አስተማማኝ ሀገር ሆና በመገኘቷ ብቻ አይደለም ይህን ማለት የሚቻለው። ከሞላ ጎደል ከምዕራቡ ጉድኝት አንጻር   በስልታዊ ተባባሪነት አብሮ መቆም የሚለው አቋም በየጊዜው በጥሞና ነው ጎልቶ የሚነገረው።እንደእኔ አመለካከት  ፣ ቻይና  እዚህ ላይ ለጥቅሟ የትም  ቦታ ማትኮር እንደምትችል  ምዕራቡን  ዓለም ማስገንዘቧ ወይም  ምልክት መስጠቷ ነው።  የጠቅላላው ዲፕሎማሲ  መልእክትም ይኸው ነው »

China Xi Jinping mit Putin in Moskau 22.03.2013

ሺን ና ፑቲን

የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የዛሬ 1 አመት ገደማ ቻይናን ከመጎብኘታቸው በፊት በአንድ ፅሁፋቸው ላይ ዋናው ጉዳይ ማንኛውም አስተዋይ ፖለቲከኛም ሆነ  የምጣኔ ሃብት ሊቅ ነኝ የሚል  ዓለም ዓቀፉ ግንኙነትን በሚያስብበት ጊዜ በአሁኑ ዘመን ከሩስያና ከቻይና በስተጀርባ ከሁለቱ አገሮች ጥቅም ውጭ ዓለም ዓቀፍ አጀንዳ ይዞ መራመድን  ማሰብ አይቻልም  ብለው ነበር ። ይህም ለምሳሌ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በግልፅ ታይቷል ።  ቻይና በምክር ቤቱ ድምፅ አሰጣጥ ላይ በአመዛኙ ከሩስያ ጎን ትቆማለች ። የቻይናን ጥቅም ያን ያህል በማይጋፋው በኢራንም  ሆነ በሩስያ ጉዳይ ላይ ቻይና ከሩስያ ጋር ተመሳሳይ አቋም ነው የያዘችው ። በሌላ በኩል  ቻይና ምስራቅ እስያ ውስጥ ተፅእኖ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ የሩስያን ድጋፍ ትጠብቃለች ። የቦን ዩኒቨርስቲ ባልደረባ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር ጉ ዜዉ ፣ እንደሚሉት በአሁኑ የፕሬዝዳንቱ  ጉብኝት የሁለቱ አገራት ስልታዊ ግንኙነት የንግግራቸው ዋነኛ ትኩረት ነው። «የመጀመሪያው  ስሌት፤ ከሩሲያ ጋር በስልታዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም ለመያዝ መስማማቱ ላይ ነው። በዛ ያሉ ችግሮች ፣ መፍትኄዎች እንዲገኝላቸው መላ መሻት ያስፈልጋል። ከጃፓን ጋር ያለው ውዝግብ፤ በኮሪያው ልሳነ-ምድር የተባባሰው የፀጥታ ይዞታ፣ የኢራንም ጉዳይ ቢሆን ፤ ሞስኮና ቤይጂንግ መላ የሚፈልጉለት አንገብጋቢ ርእስ ነው።  ሁለተኛ፤ ሁለቱም ወገኖች፤ በተለይ ሩሲያ ፣ የንግዱን ይዞታ ይበልጥ የማስፋፋት መዋቅሩንም ይበልጥ የማድረጀት ፍላጎት ነው ያላት። »

China Xi Jinping in Moskau 22.03.2013

ሺንna ባለቤታቸው ፔንግ ልዮዋን

እንደ ጉ ሁለቱ አገሮች የንግድን ወታደራዊ ትብብርን  ይበልጥ ለማጠንናከርም አልመዋል ። ይህን የሚያደርጉት አሜሪካን ፊቷን ወደ እስያ በመመለሷ ነው ። የቻይናና የሩስያ የንግድ ግንኙነት ባለፉት 2 አመታት በ 40 በመቶ አድጓል ። እጎአ በ2011 83.5 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር ። ከዚያ በቀደመው አመት ደግሞ ቻይና የጀርመንን ቦታ በመውሰድ ትልቋ የንግድ አጋር ነበረች ። ሩስያ ግን በሁለቱ አገራት የንግድ መዋቅር ደስተኛ እትረካም ። ሩስያ ለቻይና የምትነግደው ጥሬ እቃዎች ሲሆን ከቻይና ወደ ሩስያ የሚገባው ግን  ዘመናዊ ና ጥራት ያለው  የኢንዱስትሪ  ምርት ነው   ።  የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ጉ ቻይና በፋንታዋ ከሩስያ የሚያስፈልጋት ድጋፍ አለ ይላሉ

«ቻይና ውስጥ ፣ የኑክልየር ኃይል ምንጭ  ገበያ እጅጉን እየተስፋፋ ነው። ምክንያቱም የቻይና መንግሥት ለኃይል ምንጭ ጠቀሜታ ሌላ አቅጣጫ መያዝ ጀምሯልና። ይበልጥ ያተኮረውም በኑክልየር የኃይል ምንጭ ላይ ሆኗል። ይሁንና ፣ ቻይና  ፣ በአሁኑ ጊዜም ቢሆን  በሌሎች የኑክልየር  ቴክኖሎጂ የምትመካ ሀገር ናት፤ በተለይ ታላላቅ የኑክልየር ኃይል ማመንጫ አውታሮችን በመትከል ረገድ። በዚህ ዘርፍ ደግሞ፤ ሩሲያ ለማገዝም ሆነ ለማቅረብ ዝግጁ ናት።»

ማትያስ ፎን ሃይን

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic