የሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ ንረትና እጥረት | ኢትዮጵያ | DW | 15.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ ንረትና እጥረት

ነዋሪው ኑሮ ከበደን ይላል። የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ መጠን መጨመሩ ሳያንስ ከገበያ ጠፉ ሲል ያማርራል። መንግስት የዋጋ መጨመር ከዓለም ዓቀፍ ገበያ ጋር የተያያዘ ነው ይላል።

default

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተንቀሳቃሽ ስልክና በኢሜይል ከሚደርሱን መልዕክቶች አብዛኞቹ በኢትዮዽያ ከዕለት ወደዕለት እየጨመረ በመጣው የሸቀጦች ዋጋ ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። በተለይም መሰረታዊ የምግብ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ የመኖር ህልውናችንን እያናጋው ነው። መፍትሄ የሚሰጥ አካል ካለ አነጋግሩልን የሚሉ መልዕክቶች በብዛት እየደረሱን ነው። ስኳርና ዘይት ዋጋቸው መጨመሩ ሳያንስ ጭራሽ ከገበያ ሊገኙ አልቻሉም ሲሉም አንዳንድ ነዋሪዎች በምሬት ይገልጻሉ። የነዋሪውን አስተያየቶች በመያዝ ያነጋገርናቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣን፤ የዋጋው መጨመር ከዓለም ዓቀፍ ዋጋ መጨመር ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ገልጸዋል። መንግስት ችግሩን ለመቅርፍ እየሰራ ነው ሲሉም ተናግረዋል። መሳይ መኮንን የአንዳንድ ነዋሪዎችን አስተያየቶቸ በመሰብሰብ የመንግስትን ምላሽ ያካተተ ዘገባ አዘጋጅቷል። ቀጥሎ ይቀርባል።

መሳይ መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ

ተዛማጅ ዘገባዎች