የሶርያ ውዝግብና የዓለም ሀገሮች | ዓለም | DW | 30.05.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሶርያ ውዝግብና የዓለም ሀገሮች

የሶርያ ልዩ ልዑክ የቀድሞው የተመድ ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የሶርያ ፕሬዚደንት በሺር ኧል አሳድ አሥራ አምስት ወር የሆነውን ደም አፋሳሽ ውዝግብ ባስቸኳይ እንዲያበቁ አሳሰቡ። ባለፈው ዓርብ በሁላ ከተማ ቢያንስ አንድ መቶ ሰዎች የተገደሉበትን ርምጃ

በመቃወም ጀርመን፡ ፈረንሣይና በርካታ የአውሮጳ ህብረት ሀገሮች፡ እንዲሁም፡ ዩኤስ አሜሪካ፡ ካናዳ፡ አውስትሬሊያ፡ ቱርክና ጃፓን የሶርያ አምባሳደሮችና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በሰባ ሁለት ሰዓት ሀገሮቻቸውን ለቀው እንዲወጡ አዘዋል። የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ኡልሪኽ ላይድሆልት እንደሚለው፡ ምዕራባውያቱ ሀገሮች ይኸው ያጠናከሩት ግፊት የአሳድ መንግሥት በተቃዋሚዎች ላይ እየወሰደ ያለውን የኃይል ርምጃ እንዲያበቃ ማስቻሉን ብዙዎች ይጠራጠሩታል።

ትናንት በደማስቆ ከሶርያ ፕሬዚደንት በሺር ኧል አሳድ ጋ የተወያዩት የሶርያ ልዩ ልዑክ ኮፊ አናን የሶርያ መንግሥት ደም አፋሳሹን ግጭት አሁኑኑ እንዲያበቃ እና አሳድም ውዝግቡን ለማብቃት አናን ያዘጋጁትን ባለስድስት ነጥብ የሰላም ዕቅድ ተግባራዊ የማድረጉን ቆራጥ ርምጃ ነገ ሳይሆን ዛሬውኑ እንዲወስዱ አሳስበዋል። በውዝግቡ የሚፋለሙት የጦር ኃይሉና ተፋላሚ ሚሊሺያዎችም በጠቅላላ የኃይሉን ርምጃ እንዲያቆሙና የሰላሙን ዕቅድ እውን ለማድረግ የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲያበረክቱ በጥብቅ ጠይቀዋል። ይሁንና፡ በሁላ ከመቶ የሚበልጥ ሰው የተጨፈጨፈበት ድርጊት ግን ለሶርያ ውዝግብ በድርድር መፍትሔ ማገኘቱ ምን ያህል አዳጋች መሆኑን እንዳሳየ አናን ተገንዝበውታል።


« ይህ የሰላም መልዕክት ለመንግሥቱ ብቻ ሳይሆን፡ የጦር መሣሪያ ለያዛ ማንኛውም ግለሰብ ነው። ባለ ስድስት ነጥቡ አጠቃላይ የሰላም ዕቅድ ተግባራዊ መሆን አለበት። ግን ዛሬ ይህ እየሆነ አይደለም። »

በሰላሙ ዕቅድ መሠረት የተኩስ አቁሙ ደንብ ካለፉት ሰባት ሣምንታት ወዲህ ተግባራዊ ነው ቢባልም እና የተመድ ታዛቢ ቡድን በሀገሪቱ ቢሰማራም፡ በሶርያ ግድያው አላበቃም። በዚህም የተነሳ ጀርመን፡ ፈረንሣይና በርካታ የአውሮጳ ህብረት ሀገሮች፡ እንዲሁም፡ ዩኤስ አሜሪካ፡ ካናዳ፡ አውስትሬሊያ፡ ቱርክና ጃፓን የሶርያ አምባሳደሮችና ከፍተኛ ዲፕሎማቶች ሀገሮቻቸውን ለቀው እንዲወቱ የሰባ ሁለት ሰዓት ጊዜ ሰጥተዋል። የሁላውን ዓይነት ግድያ ለማብቃት በሶርያ አንፃር ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እስከተስማማ ድረስ ወታደራዊ ርምጃ አይወሰድም ተብሎ እንደማይታሰብ የፈረንሣይ ፕሬዚደንት ፍራንስዋ ኦሎንድ አስታውቀዋል።

epa03210500 French President-elect Francois Hollande attends the V-E day ceremony commemorating the 67th anniversary of the Allied victory during WWII, at the Tomb of the Unknown Soldier under the Arc de Triomphe in Paris, France, 08 May 2012. EPA/IAN LANGSDON/POOL +++(c) dpa - Bildfunk+++

ፍራንስዋ ኦላንድ

« ወታደራዊው ርምጃ ከጥያቄ ውጭ አይደለም። ዓለም አቀፉ ሕግ እስከተከበረ ድረስ። ማለትም የተመድ ፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ከመከረ በኋላ መሆን ይኖርበታል። እኔና ሌሎች ሩስያውያኑንና ቻይናውያኑን ማግባባት፡ እንዲሁም፡ መፍትሔ ማፈላለግ ይጠበቅብናል። ይህ መፍትሔ የግድ ወታደራዊ ርምጃ መሆን የለበትም። ግን የበሺር ኧል አሳድን መንግሥት ለማስወገድ በወቅቱ ግፊቱ መጠናከር ይኖርበታል። »
ምክር ቤቱ ወታደራዊ ርምጃ የሚወሰድበትን ውሳኔ ማሳለፍ ይችል ዘንድ ግን ሩስያ እና ቻይና ዕቅዱን እንዲደግፉ ማግባባት አስፈላጊ መሆኑን ኦሎንድ አመልክተዋል።
ይሁንና፡ ቻይና እና ሩስያ ምንም እንኳን የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የሁላን ግድያ ያወገዘበትን ውሳኔ ቢደግፉም፡ በሶርያ አንፃር ማንኛውንም ወታደራዊ ርምጃ እንደማይደግፉ ግልፅ አድርገዋል። ይህ ዓይነቱ ውሳኔ ውዝግቡን ይበልጡን እንደሚያባብሰው የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትእር ሴርጌይ ላቭሮቭ ገልጸዋል።

Russian Foreign Minister Sergey Lavrov answers for a question during a news conference after his meeting with Thorbjorn Jagland, secretary-general of the Council of Europe in Moscow, Russia, Tuesday, May 17, 2011. Sergey Lavrov said Libyan government representatives told him Tuesday that Tripoli was ready to consider a peace plan of the African Union and abide by the United Nations demands if rebels do the same and NATO ends its air blitz. Lavrov said he urged Tripoli to allow the delivery of humanitarian aid. (AP Photo/Alexander Zemlianichenko)

ሴርጌይ ላቭሮቭ

« በምንወስደው ማንኛውም ርምጃ ላይ በጣም ጥንቃቄ ማድረግ ይገባናል። እሣት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ የለብንም። በዚህ ፈንታ ውዝግቡን ማብረድና ተቀናቃኞቹን ወገኖች እንደገና ወደ ድርድሩ ጠረጴዛ እንዲመለሱ ማድረግ ይጠበቅብናል። »
በኃይል የሚደረግ የሥልጣን ለውጥን በጥብቅ እንደምትቃወምም ቻይና በተጨማሪ አስታውቃለች።
ልክ እንደቻይናና ሩስያም የዐረብ ሊግ አባል ሀገሮች ወታደራዊ ርምጃን አይደግፉም። እስካሁን አንድም የሶርያን ዲፕሎማት ከሀገራቸው አላስወጡም።
በሶርያ ግድያው እንዳይቀጥል ለማከላከል ዲፕሎማቲኩን ግፊት ከማጠናከር የተሻለ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ነው የገለጹት።

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 30.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/154cd
 • ቀን 30.05.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/154cd