የሶርያ መንግሥት ከባለሥልጣናቱ የገጠመው ችግር | ዓለም | DW | 07.08.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሶርያ መንግሥት ከባለሥልጣናቱ የገጠመው ችግር

የሶርያ ጠቅላይ ሚንስትር ሪዣድ ሂጃብ የፕሬዚደንት በሻር አል አሳድ መንግሥት በራሱ ሕዝብ ላይ ያካሂደዋል ያሉትን የጀምላ ጭፍጨፋ በመቃወም በትናንቱ ዕለት ከድተው የተቃዋሚውን ጎራ መቀላቀላቸው የሚታወስ ነው። የሶርያ መንግሥት ግን ሂጃብ ከሥልጣናቸው እንደተባረሩ ነው ያስታወቀው።

Syria's former agriculture minister Riyad Hijab is seen in this file handout photograph distributed by Syrian News Agency (SANA) on June 6, 2012. Syrian Prime Minister Hijab has been sacked, Syrian television reported on August 6, 2012. Syrian President Bashar al-Assad appointed Hijab, a former agriculture minister, as prime minister in June following a parliamentary election in May which authorities said was a step towards political reform but which opponents dismissed as a sham. REUTERS/SANA/Handout (SYRIA - Tags: POLITICS CIVIL UNREST HEADSHOT) FOR EDITORIAL USE ONLY. NOT FOR SALE FOR MARKETING OR ADVERTISING CAMPAIGNS. THIS IMAGE HAS BEEN SUPPLIED BY A THIRD PARTY. IT IS DISTRIBUTED, EXACTLY AS RECEIVED BY REUTERS, AS A SERVICE TO CLIENTS

የሶርያ ጠ/ ሚንስትር ሪዣድ ሂጃብ


የውጭ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚሉት፡ የሶርያ ጠቅላይ ሚንስትር እና በሶርያ የተቃዋሚው ወገን ቃል አቀባይ ዘገባ መሠረት፡ ሁለት የመንግሥት ሚንስትሮች እና ሦስት ከፍተኛ የጦር ኃይሉ መኮንኖችም የከዱበት ድርጊት የፕሬዚደንት አሳድ መንግሥት ከውስጥ በገጠመው ተቃውሞ እየፈራረሰ መሆኑን ጠቋሚ ነው።

ይህ በዚህ እንዳለ፣ የሶርያ ፕሬዝደንት በሽር አልአሰድ ላለፉት 17 ወራት የተነሳባቸዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ ለመጨፍለቅ ቆርጠዉ መነሳታቸዉን አመለከቱ። ከሁለት ሳምንታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ያሉት አልአሰድ፤ የሶርያ ህዝብና መንግስት የአሸባሪዎችን ሀገርና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት መዘጋጀታቸዉን መግለፃቸዉን ሮይተርስ የሀገሪቱን የዜና ወኪል በመጥቀስ ዘግቧል። አልአሰድ ስለጤና ማጣታቸዉም ሆነ ስለመገደላቸዉ ሲናፈስ የነበረዉን ወሬ ለጉብኝት ደማስቆ ከሚገኙት የኢራን የከፍተኛ ብሄራዊ የደህነት ምክር ቤት ኃላፊ ሳኢድ ጃሊሊ ጋ በመሆን በቴሌቪዥን ብቅ በማለትም መሠረተ ቢስ እንደሆነ አሳይተዋል።

ነቢዩ ሲራክ
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic