የሶሪያ ጉዳይ ጉባኤ በቱኒሲያ | ዓለም | DW | 24.02.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

የሶሪያ ጉዳይ ጉባኤ በቱኒሲያ

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ቀርቦ የነበረዉን የደማስቆ መንግሥትን የሚያወግዝ ረቂቅ-ዉሳኔ ድምፅን በድምፅ በመሻር ሥልጣናቸዉ ዉድቅ ያደረጉት ሩሲያና ቻይናም በጉባኤዉ ላይ አልተካፈሉም።

ለሶሪያ ግጭትና ዉጊያ የጋራ «መፍትሔ ለመፈለግ ያለመ»-የተባለ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ዛሬ ቱኒስ-ቱኒዚያ ዉስጥ ተደርጓል።የግጭቱና ዉጊያዉ ዋናዉ ተዋኝ የሶሪያ መንግሥት ግን በጉባኤዉ ላይ አልተካፈለም።ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታዉ ጥበቃ ምክር ቤት ቀርቦ የነበረዉን የደማስቆ መንግሥትን የሚያወግዝ ረቂቅ-ዉሳኔ ድምፅን በድምፅ በመሻር ሥልጣናቸዉ ዉድቅ ያደረጉት ሩሲያና ቻይናም በጉባኤዉ ላይ አልተካፈሉም።ሊባኖስም እራስዋን ከጉባኤዉ አግላለች። ሌሎች የስልሳ ሐገራትና ድርጅቶች ተወካዮች ግን ተሰብስበዋል።የሶሪያዉ ግጭትና ቁርቁስም እንደቀጠለ ነዉ።የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ነብዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic