የሶሪያ ድብደባን በተመለከተ ቃለ መጠይቆች | ዓለም | DW | 14.04.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሶሪያ ድብደባን በተመለከተ ቃለ መጠይቆች

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፈረንሣይ እና ብሪታንያ ዛሬ ማለዳ ከ100 በላይ ሚሳይሎችን በማስወንጨፍ ድብደባ ፈጸሙ። ጀርመን በድብደባው ባትሳተፍም ድጋፏን ገልጣለች። የዛሬው ድብደባን በተመለከተ የጀርመን ፖለቲከኞች ምን አሉ? የመካከለኛው ምሥራቅ እና ዓረብ ሃገራትስ?

አውዲዮውን ያዳምጡ። 05:57

የሶሪያ መደብደብን በተመለከተ ቃለ መጠይቅ ከበርሊን

ዩናይትድ ስቴትስ፣ ፈረንሣይ እና ብሪታንያ ዛሬ ማለዳ ከ100 በላይ ሚሳይሎችን በማስወንጨፍ ድብደባ ፈጽመዋል። የሶሪያ አጋር ሩስያ ድብደባውን በማውገዝ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ጥበቃ አስቸኳይ ስብሰባ እንዲያደርግ ጥሪ አስተላልፋለች። በአስቸኳይ ስብሰባው ግን ሩስያ ድብደባው እንዲወገዝ ያቀረበችው ጥያቄ 8 ለ3 በኾነ ድምፅ ውድቅ ኾኗል። ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ሦስቱ ሃገራት ሩስያን በሚሳይል የደበደቡን የበሽር አል አሳድ መንግሥት መርዛማ ንጥር ጦር መሣሪያዎችን ተጠቅሟል በሚል ነው። ድብደባው ተፈጸመ የተባለውም ንጥረ ነገሮቹ ተከማችተው ይገኙባቸዋል በተባሉ ሥፍራዎች እንደኾነ ተገልጧል። ጀርመን በድብደባው ባትሳተፍም ድጋፏን ገልጣለች። የዛሬው ድብደባን በተመለከተ የጀርመን ፖለቲከኞች ምን አሉ? የመካከለኛው ምሥራቅ እና ዓረብ ሃገራትስ?  

ቃለመጠይቆቹን ከታች በሚታዩት የድምፅ ማእቀፎች ውስጥ ይገኛሉ።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ይልማ ኃይለሚካኤል

ስለሺ ሽብሩ

Audios and videos on the topic