የሶሪያ ተኩስ አቁም | ዓለም | DW | 13.09.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

የሶሪያ ተኩስ አቁም

ስምምነቱን የሶሪያ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ሲቀበለዉ በምዕራባዉያንና በአረብ ሐገራት የሚደገፉት አማፂያን ግን ስምምነቱን ቢቀበሉትም ስምምነቱ ለሶሪያ መንግሥት ያዳላ ነዉ በማለት ሲያንገራግሩ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:57

የሶሪያ ተኩስ አቁም

የሶሪያን ተፋላሚ ሐይላት የሚረዱት ዩናይትድ ስቴትስና ሩሲያ በሳምንቱ ማብቂያ ያወጁት ተኩስ አቁም እስካሁን ከሞለ ጎደል ተግባራዊ መሆኑ እየተዘገበ ነዉ።የተለያዩ መገናኛ ዜዴዎች እንደዘገቡት ከትናንት ጀምሮ ገቢራዊ የሆነዉ ተኩስ አቁም አልፎ አልፎ ቢጣስም በአብዛኞቹ አካባቢዎች የተኩስ ልዉዉጡ እንደቆመ ነዉ።የተኩስ አቁም ሥምምነቱን የሶሪያ መንግሥት ሙሉ በሙሉ ሲቀበለዉ በምዕራባዉያንና በአረብ ሐገራት የሚደገፉት አማፂያን ግን ስምምነቱን ቢቀበሉትም ስምምነቱ ለሶሪያ መንግሥት ያዳላ ነዉ በማለት ሲያንገራግሩ ነበሩ።በዚሕም ምክንያት ስምምነቱ እንደከዚሕ ቀደሞቹ ስምምነቶቹ ሁሉ መፍረሱ አይቀርም የሚል ግምት አሳድሯል።የብራስልሱ ወኪላችን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic