የሶማልያ ጦር ፀረ አሸባብ ትግል | አፍሪቃ | DW | 15.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

የሶማልያ ጦር ፀረ አሸባብ ትግል

የሶማሊያ ጦር እና የአፍሪቃ ኅብረት ሰላም አስከባሪ ጓድ፣ አሚሶም ወታደሮች ባለፈው እሁድ አንድ ከፍተኛ የአሸባብ አዛዥ እና ሁለት የቡድኑን አባላት በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ሀገሪቱ መረጋጋት ለማስገኘት የጀመረችውን ፖለቲከዊ ዓላማ ማሳካት ላይ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ተገለጠ።

«ዴ ፔ አ» የተሰኘዉ የጀርመን ዜና አገልግሎት ባለፈው ሰኞ የሶማሊያን የስለላ ተቋም ምንጮች ጠቅሶ ባወጣው ዘገባ አንድ የአሸባብ ኮማንደር እና ሁለት የቡድኑ ከፍተኛ አባሎች በሶማሊያ እና በአፍቃ ህብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ቁጥጥር ስር መዋላቸዉን አስታውቋል።
ሶስቱም በሶማልያ መንግሥት አንፃር የሚዋጋው ቡድን አባላት የተያዙት ባለፈዉ እሁድ ምሽት ኤልቡር በምትባለዉ ከተማ አቅራብያ ነበር። ዩሱፍ ወይም አል ጋኔይ በመባል የሚታወቁት ከፍተኛ የአሸባብ ኮማንደር ሲቪሉን ህዝብ በመግደል እና ሶማሊያ እና በአፍቃ ህብረት የሰላም አስከባሪ ወታደሮች ላይ ጉዳት በማድረስ እንደሚታወቁ የሶማሊያ የጦር አዛዥ ሞሃመድ ካህዬ ተናግረዋል።

የሶማልያ ጦር በአሸባብ ላይ የሚያስመዘግበው ማንኛውም ድል ሀገሪቱን ለማረጋጋት የተጀመረውን የፖለቲካ ሂደት ወደፊት ለማራመድ አዎንታዊ ድርሻ እንደሚያበረክት የዓለም አቀፉ የጸጥታ ጥናት ተቋም ተንታኝ አቶ ሃሌሉያ ሉሌን ለዶይቼ ቤሌ ረድዮ ተናግሮዋል።
ነገር ግን ቀደም ሲል የተዘረዘሩት ሶስት ጉዳዮች ሊሳኩ የሚችሉት የአሸባብ ተዋጊዎችን በመማረክ ብቻ ሳይሆን በፖለቲካዊው እና በማህበራዊው ዘርፎች የሚታዩ እንቅስቃሴዎች በተጨማሪ ዉጤታማ ሲሆኑ ነዉ ይላሉ የዓለም አቀፉ የጸጥታ ጥናት ተቋም ተንታኝ አቶ ሃሌሉያ ሉሌ።
ይህ በዚህ እንዳለ፣ በማዕከላይ ሶማልያ በጋልሙዱግ አካባቢ የአማራ ከተማ ከሶማልያ ጦር ጋር በተካሄደ ውጊያ በርካታ የአሸባብ ሚሊሺያዎች መገደላቸውን አንድ ያካባቢው ባለስልጣን አስታውቀዋል።
መርጋ ዮናስ
አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic