የሶማልያ የሽግግር መንግስትና ሽኩቻው፣ | የሶማልያ ውዝግብ | DW | 05.08.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

የሶማልያ ውዝግብ

የሶማልያ የሽግግር መንግስትና ሽኩቻው፣

የሶማልያ ጠቅላይ ሚንስትር ኑር ሀሰን ሁሴን የመዲናይቱን የመቅዲሹን ከንቲባ መሀመድ ኦማር ሀቤብን ባለፈው ረቡዕ ከሥልጣን ቢያስወግዱም ከንቲባ መሀመድ ፕሬዚዳንት አብዱላሂ ዩሱፍ ካልሻሩኝ፣ ማንም ከስልጣን አያስወግደኝም እያሉ ነው።

የፈንጂ ጥቃት በሶማልያ

የፈንጂ ጥቃት በሶማልያ

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሽግግሩ መንግስት ባለስልጣናት መካከል ንትርክ ተፈጥሮ፣ ባለፈው ቅዳሜ ክ 15ቱ የሚንስትሮች ምክር ቤት አባላት 10ሩ ሥልጣን ለመልቀቅ እስከማስጠንቀቅ መድረሳቸው ነው የተነገረው።

በጸጥታው ረገድ፤ መረጋጋት ያልታየባት ሶማልያ፣ በፖለቲካው መስክም ከታመሰች ምን ይሆን የሚበጃት?

ጠቅላይ ሚንስትሩ ኑር ሀሰን ሁሴን፣ የፕሬዚዳንት አብዱላሂ ዩሱፍ ወዳጅ መሆናቸውን የሚነገርላቸውን ከንቲባ መሻራቸው፣በሽግግሩ መንግስት መካከል መቃቃር መኖሩን ጠቋሚ ነው ወይ?ከሆነስ ወደምንሊያመራ ይችላል?ተቀማጭነታቸው በናይሮቢ የሆነው የአፍሪቃው ቀንድ አካባቢ በተለይም የሶማልያ የፖለቲካ፣ የኤኮኖሚና ማኅበራዊ ኑሮ ጉዳዮች ተንታኝ፣ ምስተር ራሺድ አብዲ---

«በመጀመሪያ እንደሚመስለኝ ማለት የምንችለው፣ ይህ በጠ/ሚንስትሩና የቀድሞውን የመቅዲሹ አስተዳዳሪ በሚደግፉ መካከል የተፈጠረ የሥልጣን ሽኩቻ ስለመሆኑ ነው። ጠ?/ሚንስትሩ፣ የከተማይቱ ከንቲባ መሻራቸውን የሚያስረዳ መግለጫ፣ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት ይፋ ያደርጋሉ። ከንቲቫው ወይም የከተማይቱ አስተዳዳሪ ደግሞ(ጠ/ሚንስትሩን የማይወዱ መሆናቸው ይታወቃል) ሥልጣን እንደማይለቁ ፣ ውሳኔውንም እንደማያከብሩ ያስታውቃሉ። አሁን ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠት ሥልጣን እንደሚለቁ ያስታወቁት ሚንስትሮች የቀድሞው የመቅዲሹ አስተዳadሪ ከንቲቫ የቅርብ ወዳጅ በሆኑ ሚንስትር የተመሩ ናቸው>ይህ የለየለት የተለመደ የሥልጣን ፉክክር ሲሆን ግብግቡም፣ በጠ/ሚንስትሩና በ,ቀድሞው የመቅዲሹ አስተዳዳሪዎች ወዳጆች በሆኑ ሚንስትሮች መካከል በመካሄድ ላይ ያለ ነው። »

ሽኩቻው፣ የሥልጣን ፉክክሩ ፣ በዚያች ገና ፍጹም ባልተረጋጋች ሀገር ወደምን ሊያመራ ይችላል?

«እንደሚመስለኝ፣ በአጭር የጊዜ ሂደት፤ ትግሉ አይሎ ይቀጥላል። ፕሬዚዳንቱ ጣልቃ በመግባት ውሳኔው ያከተመለት ነው፣ የጠ/ሚንስትሩን ውሳኔ የምቀበለው ነው--በማለት ይህን እርምጃ ከደገፉ የውዝግቡ ግለት ይበርዳል። ነገር, ግን፣ ፕሬዚዳንቱ የተቃዋሚዎቹን ሚንስትሮች አቋም ከደገፉ በመጨረሻ፣ ጠ/ሚንስትሩ በፓርላማው ተዓማኒነት አላቸው-የላቸውም፣ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት መካሄዱ የማይቀር ይሆናል።

ተዛማጅ ዘገባዎች