1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሶማሊያ ካቢኔ ሹምሽር

ሰኞ፣ ሰኔ 28 2002

ከሚሊሺያ ቡድን ሁለት ሚኒስትሮች ተሹመዋል። አዲሱ ካቢኔ በሶማሊያ ምክር ቤት መጽደቁ አጠራጣሪ በሆነበት በአሁኑ ጊዜ በአህሉ ሱኒ ዋል ጀማ ቡድን ውድቅ ተደርጓል።

https://p.dw.com/p/OBAD
ጠቅላይ ሚኒስትር ሸርማርኬምስል AP

ጠቅላይ ሚኒስትር ኦማር አብዲረሺድ ዓሊ ሼርማርኬ ሦስት ወራት የወሰደባቸውን የሹም ሽር ውሳኔ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ተግባራዊ ሲያደርጉ የሶማሊያ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ወደ ሰላሙ ያመራ ይሆን --የሚል ተስፋ በብዙዎች ዘንድ አጭሮ ነበር። የካቢኔ ሹምሽሩ በሸርማርኬና በፕሬዝዳንቱ በሼክ ሸሪፍ መሓል ያለውን የሻከረ ግንኙነትንም ሳያለሳልሰው እንዳልቀረ ተገምቷል። በዚህ የካቢኔ ሽግሽግ ሁለት ተደማጭነት ያላቸው ለዘብተኛ የሚሊሺያ መሪዎች በሚኒስትርነት ተሹመዋል።የአህሉ ሱኒ ዋል ጀማ ቡድን አባል የሆኑት ሁለቱ ሰዎች አዲሱን ካቢኔ ተቀላቅለዋል። ጋዜጠኛ ሞሀመድ ሐጂ አብዲኑር እንደሚለው ግን አዲሱ ካቢኔ ገና በምክር ቤት የሚገጥመው ፈተና እያለ ከሱኒ መሪዎች የደረሰበት ተቃውሞ የካቢኔውን ስኬታማነት አጠራጣሪ አድርጎታል። አህሉ ሱኒ ዋል ጀማ በአዲሱ ካቢኔ የተካተቱት ሁለቱ ሰዎች አንደማይወክሉት ገልጿል።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ