የሶማሊያ አማፂ ቡድን መሪ ጉዞና የቡድኑ ማስተባበያ | ኢትዮጵያ | DW | 02.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

የሶማሊያ አማፂ ቡድን መሪ ጉዞና የቡድኑ ማስተባበያ

አዌስ ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ተስማሙ መባሉን ጃማዕ የአዉሮጳ ፕሮፓጋንዳ ብለዉታል

default

የሶማሊያ ደፈጣ ተዋጊዎጭ

ሕብረት ለሶማሊያ ዳግም ነፃነት (በእንግሊዝኛ ምሕፃሩ ARS) የተሰኘዉ አማፂ ቡድን መሪ ሼክ ሐሰን ዳሒር አዌስ ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ሳይስማሙ አይቀሩም የሚለዉን ዘገባ መንበሩን አስመራ ያደረገዉ ቡድን አንድ ባለሥልጣን አስተባባሉ።ዩናይትድ ስቴትስና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በአሸባሪነት የፈረጇቸዉ ሼኽ ዳሒር አዌስ በካርቱም በኩል ወደ መቅዲሾ መጓዛቸዉን የዜና ወኪሎች ትናንት ዘግበዉ ነበር።የኤ አር ኤስ ሥራ-አስፈፃሚ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ጃማዕ መሐመድ ዛሬ በተለይ ለዶቼ ቬለ እንደነገሩት ሼክ ዳሒር አዌስ ካርቱም መሔዳቸዉ እዉነት ነዉ።ከሶማሊያ መንግሥት ጋር ተስማሙ መባሉን ግን ጃማዕ የአዉሮጳ ፕሮፓጋንዳ ብለዉታል።ጎይቶም ቢሆን ከአስሥመራ።